የኢትዮጵያ ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን አዲስ አበባ ስታዲዬም አካባቢ ከግዮን ሆቴል ጎን ካለው የሚድሮክ ናኒ ሕንጻ አጠገብ የሚገኘውን ሕንጻ ለቢሮ አገልግሎት ለመጠቀም የሕንጻ እድሳት አድርጎ የጨረሰ ሲሆን፤ በሕንጻ ስር የሚገኝ አንድ ክፍል ለንግድ ሥራ ወይም ለቢሮ አገልግሎት ለማከራየት ይፈልጋል፡፡
በድጋሚ የወጣ የንግድ ቤት ኪራይ የጨረታ ማስታወቂያ
ጨረታ ቁጥር ብግጨ/ኢኢኮ/R01/2018
የኢትዮጵያ ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን አዲስ አበባ ስታዲዬም አካባቢ ከግዮን ሆቴል ጎን ካለው የሚድሮክ ናኒ ሕንጻ አጠገብ የሚገኘውን ሕንጻ ለቢሮ አገልግሎት ለመጠቀም የሕንጻ እድሳት አድርጎ የጨረሰ ሲሆን፤ በሕንጻ ስር የሚገኝ አንድ ክፍል ለንግድ ሥራ ወይም ለቢሮ አገልግሎት ለማከራየት ይፈልጋል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሠነዱን ከታች በተገለፀው አድራሻ ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ታኅሣሥ 23 ቀን 2018ዓ.ም. ከቀኑ 4፡00 ሰዓት ድረስ ለዚህ ጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ማስገባት ይችላሉ፡፡ ዘግይተው የቀረቡ የጨረታ መልሶች ተቀባይነት የላቸውም፡፡ በጨረታው ላይ ለመገኘት በፈለጉ ተጫራቾች ወይም የተጫራቾች ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጨረታው ታኅሣሥ 23 ቀን 2018 ዓ.ም በ4፡30 ሰዓት ይከፈታል።
- ከጨረታ ሰነድ ጋር የታደሰ ንግድ ፈቃድ እና ቲን ሰርተፍኬት መያያዝ አለበት፡፡
- በጨረታው ቅድሚያ ክፍያ ለስድስት (6) ወር እና ከዚያ በላይ ቅድሚያ ክፍያ ለሚሰጡ ድርጅቶች ቅድሚያ ይሰጣቸዋል፡፡
- የጨረታ አሸናፊዎች የኪራይ ውል መዋዋል የሚችሉት ለጨረታ ባስገቡት የንግድ ፈቃድ ስም ብቻ ነው።
- በጨረታ ያሸነፉበትን ከፍል በምንም ዓይነት ለሌላ ወገን ስም ማዞርም ሆነ ተከራይቶ ማከራየት የማይቻል ሲሆን፤ ይህንን ለማድረግ የሚሞከሩ ተጫራቾች ከጨረታ ውጪ እንደሚሆኑ እና የኪራይ ውሉ እንደሚሰረዝ ለማሳሰብ እንወዳለን፡፡
- ፍላጎት ያላቸው ተጫራቾች የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ለመግዛት ከዚህ በታች በተገለፀው አድራሻ የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ ብር) በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሂሳብ ቁጥር 1000237347262 ገቢ በማድረግ የባንክ ደረሰኝ ይዘው በመምጣት ወይም በአካል ቀርበው በመከፈል የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ የጨረታ ማስከበሪያ መጠን ብር 30,000.00 (ሰላሳ ሺህ ብር) በሲፒአ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሠረተ የባንከ ዋስትና አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።
- ይህ የጨረታ መጋበዣ ሰነድ የሚያካትተው የሚከራየውን ቦታ ዝርዝር እና የሚከራየውን ቦታ በካሬ የሚያሳይ ዲዛይን ይሆናል፡፡
- ይህ የኪራይ አገልግሎት ጨረታ ታሳቢ የሚያደርገው በሀገር ውስጥ ለሚፈፀም የአገልግሎት ሽያጭ (የምክር አገልግሎትን አይጨምርም) የሚውል መደበኛ የጨረታ ሰነድ ይሆናል፡፡
- ኮርፖሬሽኑ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
አድራሻ፡-
የኢትዮጵያ ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን (ኢ.ኢ.ኮ.) ሕንጻ 1 አራተኛ ፎቅ፡ በኮርፖሬት አገልግሎቶች የግዥ ቡድን ቢሮ፣ ከመገናኛ አደባባይ ወደ ኢትዮጵያ አየር መንገድ በሚወስደው ዋና ቀለበት መንገድ ወደ አደይ አበባ ስታዲየም (የኢትዮጵያ ወጣቶችና ስፖርት ማዕከል) የሚያስገባው መገንጠያ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት የሚሰጥበት ሕንጻ ቦሌ ከፍለ ከተማ ወረዳ 05 ስልክ ቁጥር +251 116187446
አዲስ አበባ
የኢትዮጵያ ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን
