የሚ/አ/ከ/አስ/ር ፋይናንስ ጽ/ቤት በለሚ/አ/ከ/አስ/ር ዋና ማዘጋጃ ቤት አገ/ት በመስጠት ላይ የሚገኙ ተሽከርካሪዎች ማለትም ፋዎ ገልባጭ መኪና፣ ሲኖትራክ ገልባጭ መኪና፣ ካማ መኪና ሎደር ማሽን እና ግሬደር ማሽን በጨረታ አወዳድሮ ማስጠገን ይፈልጋል፡፡
የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ
የሚ/አ/ከ/አስ/ር ፋይናንስ ጽ/ቤት በለሚ/አ/ከ/አስ/ር ዋና ማዘጋጃ ቤት አገ/ት በመስጠት ላይ የሚገኙ ተሽከርካሪዎች ማለትም ፋዎ ገልባጭ መኪና፣ ሲኖትራክ ገልባጭ መኪና፣ ካማ መኪና ሎደር ማሽን እና ግሬደር ማሽን በጨረታ አወዳድሮ ማስጠገን ይፈልጋል፡፡ ጨረታ መወዳደር የምትፈልጉ ተጫራቾች የሚከተሉትን መስፈርቶች በማሟላት መወዳደር ይችላል፡፡
- ተጫራቾች በተሰማሩበት የሥራ መስክ የዘመኑን ግብር የከፈሉና የታደሰ የንግድ ፈቃድ እና የሥራ ፍቃድ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ቲን ነበር ተመዝጋቢ የሆኑ፡፡
- የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ መሆን አለባቸው።
- ከትንስፖርት ቢሮ የተሰጠ ደረጃውን የሚገልፅ ማስረጃ ማቅረብ የሚችል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ በግዥ ንብ/አስ/ር ቢሮ በመቅረብ ሰነዱን በነፃ በመውሰድ መወዳደር ይችላሉ።
- የጨረታ ሰነዱን ሞልተው ሲመልሱ ህጋዊነት ሰነድ እና ፋይናንሻል የተሞላበትን ሰነድ 1 ኦርጅናልና 1 ኮፒ በአንድ እናት ፖስታ በማሸግ ለዚሁ በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት አየር ላይ የሚቆይ ሆኖ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ በ3፡30 ታሽጎ በዚያው ቀን በ4፡00 ሠዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የሚከፈት ሆኖ የሚታሸግበትም ሆነ የሚከፈትበት ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ይሆናል፡፡
- ሰነዱን ሞልተው ወደ ጨረታ ሳጥን ለማስገባት ሲመጡ ተመዝግበውና ፈርመው ማስገባት አለባቸው።
- በጨረታ ማስታወቂያ ላይ የቃላት ወይም የትርጉም ስህተት ቢኖር በጨረታ ሠነዱ ላይ የተቀመጠው የበለጠ ተቀባይነት ይኖረዋል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
የሚዛን አማን ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት
