የሚ/አ/ከ/አስ/ር ፋይ/ኢ/ል/ጽ/ቤት በ2018 በጀት ዓመት በሚ/አ/ከ/አስ/ር ስር ለሚገኙ ሴ/መ/ቤቶች አገ/ት የሚውሉ ፈርኒቸር ዕቃ እና ሞተር ሳይክል በጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል፡፡
ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
የሚ/አ/ከ/አስ/ር ፋይ/ኢ/ል/ጽ/ቤት በ2018 በጀት ዓመት በሚ/አ/ከ/አስ/ር ስር ለሚገኙ ሴ/መ/ቤቶች አገ/ት የሚውሉ፡-
- ሎት 1 ፡- ፈርኒቸር ዕቃ
- ሎት 2 ፡- ሞተር ሳይክል በጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል፡፡
በዚሁ መሰረት በጨረታው መወዳደር የምትፈልጉ ተጫራቾች የሚከተሉትን መስፈርቶች በማሟላት መወዳደር ይችላል፡፡
- ተጫራቾች በተሰማሩበት የሥራ ዘርፍ የዘመኑን ግብር የከፈሉና የታደሰ ንግድ ፈቃድ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ መሆን አለባቸው፡፡
- በተሰማሩበት የሥራ ዘርፍ የአቅራቢነት ምዝገባ ሰርተፍኬት ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ተመዝጋቢ መሆን አለባቸው።
- ግብር ስለመከፈላቸው ከገቢዎች መ/ቤት ክሊራንስ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- የጨረታ ሰነድ ከግዥ ኬዝ ቲም የሥራ ሂደት ቢሮ በመቅረብ ሰነዱን /በነጻ/ በመውሰድ መወዳደር ይችላሉ።
- የጨረታ ሰነዱ ሞልተው ሲመልሱ ህጋዊነት ሰነድ እና ፋይናንሻል የተሞላበትን ሰነድ 1 ኦርጅናልና 1 ኮፒ በአንድ እናት ፖስታ በማሸግ ለዚሁ በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- የጨረታ ማስከበሪያ 10,000 /አስር ሺ ብር/ ከታወቀ ባንክ የሚሰጥ የተረጋገጠ ቼክ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና እና በባንክ የተረጋገጠ ሌተርኦፍ ከሬዲት ለሚ አ/ከ/አስ/ርፋይናንስ ጽ/ቤት በማለት ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት አየር ላይ የሚቆይ ሆኖ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ በ3፡30 ታሽጎ በዚያው ቀን በ4፡00 ሠዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የሚከፈት ሆኖ የሚታሸግበትም ሆነ የሚከፈትበት ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ይሆናል፡፡
- ሰነዱን ሞልተው ወደ ጨረታ ሳጥን ለማስገባት ሲመጡ ተመዝግበውና ፈርመው ማስገባት አለባቸው።
- በጨረታ ማስታወቂያ ላይ የቃላት ወይም የትርጉም ስህተት ቢኖር በጨረታ ሠነዱ ላይ የተቀመጠው የበለጠ ተቀባይነት ይኖረዋል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
የሚዛን አማን ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት
