መ/ቤታችን የጌዴኦ ልማት ማህበር የ2025 መደበኛ ሂሳብ የውጪ አዲት መ/ቤቶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለማስመርመር ይፈልጋል፡፡
የጨረታ ማስታወቂያ
መ/ቤታችን የጌዴኦ ልማት ማህበር የ2025 መደበኛ ሂሳብ የውጪ አዲት መ/ቤቶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለማስመርመር ይፈልጋል፡፡
በዚህ ጨረታ ለመወዳደር የምፈልጉ የኦዲት መ/ቤቶች የታደሰ የኦዲት የንግድ ሥራ ፍቃድ ያለው፣ የሙያ ብቃት ማረጋገጫ ፍቃድ ያለው፣ የዘመኑን ግብር የከፈለ፤ የሥራ ልምድ የሚገልጽ ማስረጃ ማቅረብ የሚችል፤ የቲን ቁጥር ያለው፤ በሲቪክ ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለሥልጣን የተመዝገበ እና እውቅና ያለው፤ ድርጅቱ ሂሳብ የሚመረምርበትን ዋጋ እና ሥራውን ሰርቶ ለማቅረብ የሚያስፈልገውን ጊዜ የሚገልጽ ደብዳቤ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡ በጨረታ መወዳደር የሚፈልግ ማንኛውም ድርጅት ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ15 ተከታታይ ቀናት ጊዜ ውስጥ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በፖስታ ቤት ሣ.ቁ 350 መላክ የሚችል ሲሆን በአካል መጥቶ ለማስረከብ የሚፈልግ ድርጅት ካለ በጌዴኦ ዞን በዲላ ከተማ ቡኖ ቀበሌ ከሕዝብ ላይብረሪ ጀርባ ባለው ዋና ጽ/ቤታችን በአካል በመቅረብ ገቢ ማድረግ የሚችሉ መሆኑን እንገልፃለን።
ለተጨማሪ መረጃ፡- በስልክ ቁጥር 046334375/0916930815 ይደውሉ፡፡ ጨረታው ተጫራቾች በተገኙበት ከጨረታው መዝጊያው በሚቀጥለው የሥራ ቀን በ4፡30 ሰዓት ዲላ በሚገኘው ጌዴኦ ልማት ማኅበር ዋና ጽ/ቤት በግልጽ ይከፈታል፡፡ መ/ቤታችን የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፈልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
የጌዴኦ ልማት ማኅበር
