Tender Detail

Tender Details

  • Company የሀዋሳ ከተማ መጠጥ ውሃ እና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት
  • Address , Phone: 046-212 1580
  • Website
  • Deadline16 Jan 2026, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price1000.00
  • opening date2026-01-16 00:00:00
  • Categories Accounting & Auditing , Finance

የሀዋሳ ከተማ መጠጥ ውሃ እና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት ከ2006 በጀት ዓመት ጀምሮ እስከ 2013 በጀት ዓመት ድረስ ያለውን በድርጅቱ የተንቀሳቀሰውን ንብረት በውጭ የሂሳብ አዋቂዎች የእስቶክ ምዝገባና ሪፖርት የማቅረብ አገልግሎት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል፡፡


 

በድጋሚ የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

የእስቶክ ምዝገባና ሪፖርት ማቅረብ ገልግሎት

የግዥ ቁጥር የእሥ/06/2017

 

የሀዋሳ ከተማ መጠጥ ውሃ እና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት 2006 በጀት ዓመት ጀምሮ እስከ 2013 በጀት ዓመት ድረስ ያለውን በድርጅቱ የተንቀሳቀሰውን ንብረት በውጭ የሂሳብ አዋቂዎች የእስቶክ ምዝገባና ሪፖርት የማቅረብ አገልግሎት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም ከላይ በተጠቀሱት የአገልግሎት ዘርፎች የታደሰ የንግድ ፍቃድና የውጭ የሂሳብ አዋቂዎች ማሟላት ያለባቸው፡-

  1. በኢትዮጵያ የሂሳብ አያያዝና ኦዲት ቦርድ የሙያ ፈቃድ የተሰጠው እና 2017/2018 / ህጋዊ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸው
  2. የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ ስለመሆናቸው የሚገልፅ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ እና የንግድ ፍቃድ መለያ ቁጥር (TIN No.) ያላቸው
  3. ተጫራቾች የጨረታውን ዝርዝር መረጃ የያዘ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 1,000 (አንድ ሺህ ብር) በመከፈል ከድርጅቱ ዋና ቢሮ ሦስተኛ ፎቅ ላይ ከሚገኘው የግገዢ ቡድን መሪ ቢሮ ከድርጅቱ ዋና ቢሮ 3ተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 19 ቀርበው መግዛት ይችላሉ፡፡
  4. የጨረታ ማስከበሪያ ብር 100,000.00 (አንድ መቶ ሺህ ብር) በባን የተረጋገጠ (CPO) በሀዋሳ ከተማ መጠጥ ውሃ እና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት ስም ተዘጋጅቶ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡ ከሲፒኦ ውጪ የቀረበው የጨረታ ማስከበሪያ ጨረታው ሳይከፈት ውድቅ ይሆናል፡፡
  5. ተጫራቾች በሚያቀርቡት የጨረታ ሰነዶች ላይ ስማቸው ሙሉ አድራሻቸው ፊርማቸውን አሟልተው ማቅረብ አለባቸው
  6. ተጫራቾች ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 20 ተከታታይ ቀናት እስከ ቀኑ 1100 ሰዓት ድረስ ሀዋሳ ከተማ መጠጥ ውሃ እና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት ግዥ ቡድን መሪ በመምጣት የተዘጋጀውን የጨረታ ዶክመንት መግዛት ይችላል፡፡
  7. ጨረታው የሚከፈተው ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 21ኛው ቀን ላይ ከጠዋቱ 300 ሰዓት እስከ 800 ሰዓት ድረስ ድርጅቱ ለጨረታ ባዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው ጨረታው በዕለቱ 830 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በሀዋሳ ከተማ መጠጥ ውሃ እና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት የመሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል፡፡ ሆኖም ግን 21ኛው ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ባለቤቱ ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
  8. ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው

 

የድርጅቱ አድራሻ፡-

ከሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ወይም ከወልደ አማኑኤል አደባባይ በግራ በኩል ወደ አዲሱ መናኸሪያ በሚወስደው መንገድ 200 ሜትር ገባ ብሎ ከአዜብ ዲያግኖስቲ ማዕከል አጠገብ፡፡

 

የስልክ ቁጥር 046-212-9112/ 046-2212-1580

 

የሀዋሳ ከተማ መጠጥ ውሃ እና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት

 

Save Tender