የን/ስ/ላ/ክ/ከተማ ወረዳ 10 ፋ/ጽ/ቤት የ2018 በጀት አመት አገልግሎት የሚውል እቃዎች እና አገልግሎት በግዥ መለያ ቁጥር 02/2018 በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
የጨረታ ማስታወቂያ
የን/ስ/ላ/ክ/ከተማ ወረዳ 10 ፋ/ጽ/ቤት የ2018 በጀት አመት አገልግሎት የሚውል እቃዎች እና አገልግሎት በግዥ መለያ ቁጥር 02/2018 በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለሆነም ተጫራቾች መሟላት ያለበቸው መስፈርቶች፡-
- በዘርፉ የተሰማራበት የታደሰ የንግድ ፍቃድ፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ የግብር ከፋይ ምዝገባ ሰርተፍኬት (TIN) ያላቸው፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑበት ማስረጃ፣ በአቅራቢዎች ዝርዝር የተመዘገቡና ማስረጃ ያላቸው፡፡
- የጨረታ ማስከበሪያ CPO በባንክ የተረጋገጠ በየሎቱ ሎት 1 የፅህፈት መሳርያ 1,000፣ ሎት-2 የደንብ ልብስ 2,000፣ሎት 3 የጽዳት እቃዎች 5,000፣ ሎት-4 ትራንስፖርት አገልግሎት 2,000፣ ሎት-5 ለቢሮ መስተንግዶ 1,000፣ ሎት-6 የልብስ ስፌት 1,000፣ ሎት 7 የጭነት /የጉልበት/ አገልግሎት ከተደራጁበት መ/ቤት ደብዳቤ በማፃፍ በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከተማ የወረዳ 10 ለፋይናንስ ጽ/ቤት በሚል በባንክ የተረጋገጠ CPO ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- ናሙና በተጠየቀባቸው እቃዎች /ሎት 1፣2፣3/ ላይ ጨረታ ከመከፈቱ በፊት ናሙናዉ መግባት ይኖርበታል፡፡
- የጨረታ ሰነዱ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 10ኛው የሥራ ቀን ድረስ በዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ በማስገባት ከቀኑ 11፡30 ሰዓት ተዘግቶ በ11ኛው የሥራ ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው እና ታዛቢዎች በተገኙበት በወረዳው አዳራሽ 4ኛ ፎቅ ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች የሚወዳደሩባቸውን እቃዎች ለእያንዳንዱ ዋጋውን ከቫት ጋር ማስቀመጥ ይጠበቅባቸዋል።
- የዘገየ ጨረታና በጨረታ መክፈቻ ላይ ያልተነበበ ጨረታ ተቀባይነት የለውም፡፡
- አሸናፊ ተጫራቾች ያሸነፉባቸውን እቃዎች በራሳቸው ትራንስፖርት ግዥ ፈፃሚው መ/ቤት ድረስ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በየሎቱ 200 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ መረጃ፡- ን/ስ/ላ/ክ/ከተማ ሳሪስ ኢካፍኮ 100 ሜትር ገባ ብሱ የወረዳ 10 አስተዳደር ህንፃ ፋ/ጽ/ቤት 3ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 15
የን/ስ/ላ/ክ/ከተማ ወረዳ 10 ፋ/ጽ/ቤት
