የፍልውሃ አገልግሎት ድርጅት ከዚህ በታች የተገለፁትን የተለያዩ አገልግሎት የሚውሉ ሱቆች በጨረታ ለማከራየት ተጫራቾች አወዳድሮ ለመጋበዝ ይፈልጋል።
ለመጀመሪያ ጊዜ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ
የፍልውሃ አገልግሎት ድርጅት ከዚህ በታች የተገለፁትን የተለያዩ አገልግሎት የሚውሉ ሱቆች በጨረታ ለማከራየት ተጫራቾች አወዳድሮ ለመጋበዝ ይፈልጋል።
በዚህ መሠረት፡-
ለመጀመሪያ ጊዜ ጨረታ የሚወጡ የንግድ ቤቶች ቦታ ኪራይ የአገልግሎት
- ሎት 1 ለፋርማሲ፣ ለባህል አልባሳት፣ ለጌጣጌጥ /ማስዋቢያ ዕቃዎች/ እንዲሁም ለውጭ ምንዛሪ ቢሮ
- ሎት 2 ለአየር መንገድ ትኬት መቁረጫ፣ ለሚኒ ማርኬት፣ ለዱቲፍሪ ዕቃዎች መሸጫ እና ለአበባ /ለስጦታ/ ዕቃ መሸጫ
- ሎት 3 ለላውንደሪ አገልግሎት
- ሎት 4 ለባንክ እና ለኢንሹራንስ አገልግሎት
ተጫራቾች የሚከተሉትን ማሟላትና ተግባራዊ ማድረግ አለባቸው።
- ማንኛውም ተጫራች ለእያንዳንዱ ሎት የጨረታ መስከበሪያ ብር 50,000.00 /ሃምሣ ሺህ ብር/ በባንክ በተረጋገጠ ቼክ (CPO) ብቻ ማስያዝ አለባቸው።
- ለሱቅ ኪራይ አገልግሎት ለጨረታ ሰነድ መግዣ የማይመለስ ብር 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ በድርጅታችን አዲሱ ፍልውሃ ሆቴል እንግዳ መቀበያ በመክፈል ከድርጅቱ ግዥ አቅርቦት ቡድን መሪ ቀርበው የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ።
- ተጫራቾች የሚሰጡት ዋጋ ከቫት በፊትና ከነቫቱ ተብሎ በኢትዮጵያ ብር መገለጽ አለበት። ተጫራቾች በጨረታ ሰነዶቻቸው ላይ ስማቸውን፣ ሙሉ አድራሻቸውን፣ ፊርማቸውንና በድርጅት ከሆነ የታደሰ ንግድ ፍቃድና ማህተም አሟልተው ማቅረብ አለባቸው።
- ጨረታው ከተከፈተ በኋላ በጨረታ ሠነድ ላይ የተሰጠን መለወጥ አይቻልም። የሱቅ ኪራይ አገልግሎት ለምን ሥራ እንደሚጠቀሙበት እና ዋጋው ፀንቶ የሚቆይበት ጊዜ በዝርዝር መገለጽ አለበት።
- ጨረታውን በሚመለከት ለማሸነፍ እንዲረዳዎት ለማንኛውም ኃላፊና ሠራተኛ መደለያ የሰጠ ተጫራች ከጨረታ የሚሰረዝ ሲሆን አሸንፎም ውል ቢዋዋል ውሉ ይሰረዛል።
- ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ ከቫት በፊት ወይም ከቫት ጋር በግልጽ በመሙላት በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ጥር 08 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ። ጨረታው በዕለቱ ከጠዋቱ 4፡30 ጠዋት ይከፈታል።
- ተጫራቾች በሚጫረቱበት ሱቅ መሠረት የተሟላ ቴክኒካል ሰነድ እና ፋይናንሸያል ሰነድ ማቅረብ አለባቸው። በተዘጋጀው የጨረታ ሰነድ /Bid document/ መሰረት የጨረታው ሰነዳችሁ ማስገባት ይኖርባችኋል። የጨ ረታው ሕጋዊ ሰነድ ለብቻው የጨረታ ማስከበሪያ CPO/ ለብቻው እና ፋይናሽያል ሰነድ ለብቻው በጨረታ ሣጥኑ ማስገባ አለባቸው።
- የሱቅ ኪራይ አገልግሎት ጨረታ ግምገማ በፋይናንሻል ሰነድ /ዋጋ/ 100% አሸናፊ የሚለይ መሆኑን ማወቅ አለባችሁ። ድርጅታችንም በሚገልፀው ዝርዝር የሱቆች ደረጃ፣ ስፋት፣ ቁጥር እና መነሻ ዋጋ በጨረታ ሰነዱ የሚሸጥላችሁ ይሆናል።
NB፡ የሚከራይ ሱቅ ከድርጅታችን የሥራ ባህሪ ውጭ የሆነ ህጋዊ ሥራ የሚሠሩ መሆን አለባቸው።
ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ በሙሉ ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ፡- ስልክ ቁጥር 0115 53 07 67/0115 15 73 37
ፍልውሃ አገልግሎት ድርጅት
