አዲስ ሚዲያ ኔትወርክ የተለያዩ እቃዎችን በግልጽ ጨረታ ተጫራቾችን አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል
የግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በጨረታ ቁጥር አ.ሚ.ኔ.በ.ግ.ጨ. 010/2018 ዓ.ም በግልፅ ጨረታ ተጫራቾችን አወዳድሮ ለመግዛት የሚፈልግ በመሆኑ፣ በጨረታ ለመሳተፍ የምትፈልጉ፡-
ሎት1 ሳምንታዊ የጋዜጣ ህትመት ግዥ በድጋሚ የወጣ
ሎት 2 የስቱዲዮ ግንባታ ግዥ
ሎት 3 የራዲዮ ተከታታይ ድራማ አገልግሎት ግዥ
ሎት 4 ከለር ፕሪንተር ከነቀለሙ ግዥ
ሎት 5 ቢል ቦርድ ግዥ
ሎት 6 ፈርኒቸር ግዥ
ሎት 7 ውሃ ግዥ
ሎት 8 የልብስ ማጠቢያና ማድረቂያ ማሽን (አውቶማቲክ) ግዥ
ሎች 9 የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ ቻርጅ ማድረጊያ እቃዎች ግዥ
በጨረታ ቁጥር አ.ሚ.ኔ.በ.ግ.ጨ. 010/2018 ዓ.ም በግልጽ ጨረታ ተጫራቾችን አወዳድሮ ለመግዛት የሚፈልግ በመሆኑ በጨረታው ለመሳተፍ የምትፈልጉ -
- በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣
- የተጨማሪ እሴት ታክስ እና ዮጉበር ከፋይነት መለያ ቁጥር የምዝገባ ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችሉና በግዥ አቅራቢነት የተመዘገቡ፣
- ተጫራቾች በሚያቀርቡት እያንዳንዱ ሰነድ እና በፖስታ ላይ የድርጅቱን ማህተምና ፊርማቸውን ማኖር ይጠበቅባቸዋል።
ተጫራቾች ለሚያቀርቡት አጠቃላይ ዋጋ ለሎት1= 50,000፣ ለሎት2=200,000፤ ለሎት3=25,000 ለሎት4=80.000፤ ለሎት5=100,000፤ ለሎት6=10,000፤ ለሎት7=20,000፤ ለሎት8=100,000 እና ለሎት9=30,000 ብር በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
- ተጫራቾች የጨረታውን ዝርዝር የሚያሳይ የጨረታ ሰነድ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 10 የሥራ ቀናት ውስጥ አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ ቢሮ ቁጥር 28 ሁለተኛ ፎቅ ለሰነዱ ክፍያ 300.00 (ሶስት መቶ ብር) በመክፈል ዘወትር በሥራ ሰዓት ቢሮ ቁጥር 6 ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ።
- ጨረታው በ11ኛው ቀን ከረፋዱ 4፡00 ተዘግቶ በዚሁ ቀን ከረፋዱ 4፡30 ተጫራቾች/ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በአዲስ ሚዲያ ኔትወርክ 8ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 108 ይከፈታል፡፡ ሆኖም ግን የተጫራቾች አለመገኘት ጨረታውን ለመክፈት አያግደውም ፡፡ የመክፈቻው ዕለት በዓል/ ዕረፍት ቀን ከሆነ በቀጣዩ የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ተዘግቶ ይከፈታል።
- ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሃሳባቸውን ዋናውንና ኮፒውን /ቴክኒካል ኦሪጅናልና ኮፒ፣ ፋይናንሻል ኦሪጂናልና ኮፒ/ በተለያየ ፖስታ በማሽግ በዚሁ ተብሎ በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይጠበቅባቸዋል።
- በአንዱ ተጫራች ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ የተከለከለ ነው።
- በጨረታ ያሸነፈ ተጫራች ከመ/ቤታችን ጋር ጨረታውን እንዳሸነፈ ካወቀበት ጊዜ አንስቶ በ15 ቀናት ውስጥ በሲፒኦ የጠቅላላ ዋጋውን 10% በማስያዝ ውል መዋዋል ይኖርበታል።
- 9.ተቋሙ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፈል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ፡-
የአዲስ ሚዲያ ኔትዎርከ 5 ኪሎ ቅድስት ማርያም ቤ/ክርስቲያን ከማህበረ ቅዱሳን ጀርባ ያለው ሕንፃ።
ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር፡- 0111 116 382 መደወል ይችላሉ።
አዲስ ሚዲያ ኔትወርክ
