የኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት የስፖርት ውድድር ውርርድ በ2015፣ 2016፣ 2017 እና 2018 በጀት ዓመት የኮሚሽን ተሰብሳቢ ሂሳቦች ላይ ልዩ ምርመራ (Special Audit) የሚያካሂድ በዘርፉ ህጋዊ የንግድ ስራ ፈቃድና ልምድ ያላቸውን የኦዲት ድርጅቶችን በግልጽ የጨረታ ማስታውቂያ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል።
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ መለያ ቁጥር ኤሎአ/005/2018
የኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት የስፖርት ውድድር ውርርድ በ2015፣ 2016፣ 2017 እና 2018 በጀት ዓመት የኮሚሽን ተሰብሳቢ ሂሳቦች ላይ ልዩ ምርመራ (Special Audit) የሚያካሂድ በዘርፉ ህጋዊ የንግድ ስራ ፈቃድና ልምድ ያላቸውን የኦዲት ድርጅቶችን በግልጽ የጨረታ ማስታውቂያ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል።
ስለዚህም በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ ድርጅቶች ሁሉ ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ላይታትሞ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ እስከ ጥር 8 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ ለዚህ ሥራ የተዘጋጀውን የጨረታ ሠነድ የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) በኢትዮጵያ ንግድ ባንክየኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት ስም በተከፈተ የባንከ ሂሳብ ቁጥር ገቢ በማድረግ ዋናውን ማስረጃ በማቅረብ የጨረታ ሰነዱን በመግዛት በጨረታው መወዳደር ይችላሉ:: ተጫራቶች በኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት ስም የጨረታ ማስከበሪያ ብር 50,000 (ሃምሳ ሺህ ብር) በሲፒኦ፣ በሁኔታ ላይያልተመሰረተ የባንከ ጋራንቲ ዋናውን ማስረጃ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማያያዝ አለባቸው::
ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዶችን የቴከኒካልና ፋይናንሻል ሰነዶችን የያዘ አንድ ዋና እና እንድ ቅጂ ለየብቻው በፖስታ በማድረግና በፅሁፍ በመለየት የታደሰ የኢትዮጵያ ሂሳብ አያያዝ እና አዲት ቦርድ (AABE/፣ የታደሰ የንግድ ስራ ፈቃድ፣ የንግድ ምዝገባ ምስከር ወረቀት፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ የምስከር ወረቀት፣ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር የምስከር ወረቀት፣ በጨረታ ለመሳተፍ የሚያገለግል ከሊራንስ፣ የመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ በአቅራቢነት ዝርዝርውስጥ የተመዘገቡበትን የምስከር ወረቀት፣ የማጭበርበር ድርጊት ላለመፈፀም ቃል የሚገባበት ቅፅ ሞልታችሁ ማህተምና ፊርማ አድርጋችሁ የመጫረቻ ሰነዳችሁን አሟልታችሁ በማቅረብና የጨረታ ማስከበሪያውን በታሸገ ፖስታ በማድረግ እስከ ጥር 8 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4:00 ሰዓት ድረስ ለዚሁ ሥራ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ገቢ ማድረግ አለባቸው::
ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በሚገኙበት ጥር 8 ቀን 2018 ከጠዋቱ
4፡30 ሰዓት ፒያሳ ጣይቱ ሆቴል አጠገብ በሚገኘው የኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት ዋና መ/ቤት ይከፈታል።አገልግሎቱ ስለጨረታው የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፣
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 011-126-78-16 ደውሎ መረዳት ይቻላል።
የኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት
