አኩፋዳ ማይክሮ ፋይናንስ ተቋም አ.ማ በዋና መሥሪያ ቤት የቢሮ ማስፋፊያ ሥራ ማሠራት ስለፈለገ በደረጃ 6 እና በላይ በጠቅላላ ሥራ ተቋራጭ፣ ሕንፃ ሥራ ተቋራጭ ወይም በአልሙኒየም እና መስታወት ሥራ በዘርፉ ከተሰማሩ ተቋራጮች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሠራት ይፈልጋል፡፡
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር AMFI 03/2018
አኩፋዳ ማይክሮ ፋይናንስ ተቋም አ.ማ በዋና መሥሪያ ቤት የቢሮ ማስፋፊያ ሥራ ማሠራት ስለፈለገ በደረጃ 6 እና በላይ በጠቅላላ ሥራ ተቋራጭ፣ ሕንፃ ሥራ ተቋራጭ ወይም በአልሙኒየም እና መስታወት ሥራ በዘርፉ ከተሰማሩ ተቋራጮች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሠራት ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም በጨረታው ለመሳተፍ፡-
- ተቋራጮች በዘርፍ የተሰማሩ ሆነው የዘመኑ የታደሰ የንግድ ሥራ ፈቃድ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ምስክር ወረቀት፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ምስክር ወረቀት፣ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት የዘመኑን ግብር መክፈላቸውን የሚያረጋግጥ ከግብር ሰብሳቢ ባለሥልጣን የተሰጠ የምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው። ከተቻለ የመልካም ሥራ አፈጻጸም ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ ቢሆን ይመረጣል፡፡
- ተጫራቾች ለሚያቀርቡት አጠቃላይ ዋጋ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የሚቀርብ 100,000.00 /አንድ መቶ ሺህ ብር/ በባንክ በተመሰከረ ሲ.ፒ.ኦ ወይም ጥሬ ገንዘብ በተከፈለበት በአኩፋዳ ማይክሮ ፋይናንስ ተቋም አ/ማ ደረሰኝ ወይም የባንክ ዋስትና እንደምርጫቸው ከዋናው የዋጋ ሰነድ ጋር ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ተቋራጮች የጨረታ ሰነዱን ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 8 (ስምንት) ቀናት ውስጥ ዘወትር በሥራ ሰዓት እስከ ቀኑ 11፡00 (አሥራ አንድ ሰዓት) ድረስ የማይመለስ 500.00 (አምስት መቶ ብር) ለአኩፋዳ ማይክሮ ፋይናንስ ተቋም አ.ማ በአሐዱ ባንክ ሒሳብ ቁጥር 0003230410101 ገቢ በማድረግ ገቢ የተደረገበትን ደረሰኝ አቅርበው ከአኩፋዳ ማይክሮ ፋይናንስ ተቋም አ.ማ ዋና መሥሪያ ቤት የሰው ሀብትና ፋሲሊቲ ዳይሬክቶሬት ቢሮ (ደብረ ብርሃን አጼ ዘርዓ ያእቆብ ሕንጻ) 4ኛ ወለል መውሰድ ይችላሉ፡፡
- ተቋራጮች የመወዳደሪያ ሃሣባቸውን የያዙ ሰነዶች የዋጋ ሰነድ ዋና እና ቅጅ ለየብቻው በሰም በታሸገ ፖስታ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ ቀናት እስከ 8ኛው ቀን ሲሆን ከቀኑ 4፡00 (አራት ሰዓት) ድረስ ብቻ ከአኩፋዳ ማይክሮ ፋይናንስ ተቋም አ.ማ ዋናው መሥሪያ ቤት የሰው ሀብትና ፋሲሊቲ ዳይሬክቶሬት ቢሮ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ማስታወቂያው በጋዜጣ በወጣ በ8ኛው ቀን 4፡00 /አራት ሰዓት/ ታሽጎ በዚያው ዕለት ከረፋዱ 4፡30 (አራት ሰዓት ተኩል) ላይ በግልጽ ተከፍቶ የተሞላው ዋጋ ተቋራጮችና ታዛቢዎች ባሉበት ይነበባል። የመክፈቻ ቀኑ በሳምንቱ የዕረፍት ቀናት ወይም ብሔራዊ በዓል ላይ ከዋለ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ከላይ በተገለፀው ሰዓት ይከፈታል። ትክክለኛው የመክፈቻ ቀን በጨረታ ሰነዱ ላይ የሚገለጽ ይሆናል/፡፡
- አሸናፊው ተቋራጭ በጨረታ ሰነዱ በተቀመጠው አግባብ ቢሮውን ለመከፋፈል አልሙኒየም እና መስታወት እንዲሁም ለሥራ የሚያስፈልጉ የመሥሪያ ዕቃዎች በራሳቸው ሙሉ ወጪ አኩፋዳ ማይክሮ ፋይናንስ ተቋም አ.ማ ዋና መ/ቤት (ደብረ ብርሃን አጼ ዘርዓ ያእቆብ ሕንጻ) አቅርበው በመሥራት ማስረከብ አለባቸው።
- ተጫራቾች በሌላ ተጫራች ዋጋ ላይ ተመስርተው የመወዳደሪያ ዋጋ ማቅረብ አይችሉም፡፡
- የጨረታው ውጤት ለአሸናፊና ለተሸናፊ ተጫራቾች በእኩል ጊዜ በጽሑፍ በተቋሙ የውስጥ ማስታወቂያ ሰሌዳና በደብዳቤ እንገልፃለን፡፡
- ተቋሙ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 011 637 66 68/011 637 64 57 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል።
አኩፋዳ ማይክሮ ፋይናንስ ተቋም አ.ማ
