Tender Detail

Tender Details

  • Company በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ አስተዳደር የዋና ስራ አስፈፃሚ ጽ/ቤት ግዥ ቡድን
  • Address ከራስ ሃይሉ መዝናኛ ማዕከል አጠገብ አዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ህንፃ ዋና ስራ አስፈፃሚ ግዥ ቡድን 5ኛ ፎቅ በግራ ክንፍ በኩል ፡ አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0118 69 38 76
  • Website
  • Deadline16 Jan 2026, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price100.00
  • opening date2026-01-16 00:00:00
  • Categories Carpets And Curtains , Textile, Garment & Leather , Event Organizing And Planning , Others , Vehicle , Cloth And Shoes , Decor Work

በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ አስተዳደር የዋና ስራ አስፈፃሚ ጽ/ቤት ግዥ ቡድን ከዚህ በታች በሎት የተከፋፈሉትን የዕቃ እና አገልግሎት ግዥዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ አገልግሎት መጠቀም ይፈልጋል፡፡


 

የጨረታ ማስታወቂያ 03/2018

 

በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ አስተዳደር የዋና ስራ አስፈፃሚ /ቤት ግዥ ቡድን ከዚህ በታች በሎት የተከፋፈሉትን የዕቃ እና አገልግሎት ግዥዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ አገልግሎት መጠቀም ይፈልጋል፡፡

  • ሎት 1- ደረጃውን የጠበቀ የቢሮ መጋረጃ ከነሙሉ አክሰሰሪዎቹ የስፌት እና የእጅ ዋጋ ጨምሮ ሰቅሎ አጠናቆ የሚያስረከብ፡፡
  • ሎት 2- የሰራተኞች ግዥ የወንድ ጉርድ ጫማ፣ የሴት ጉርድ ጫማ እና የወንድ ፑትስ ጫማ ግዥ ለመፈጸም ይፈልጋል፡፡
  • ሎት 3- የሰራተኞች ደንብ ልብስ ስፌት የእጅ ዋጋ የዓቃቤ ህግ ባለሙያዎች የችሎት ጋውን ስፌት በሚሰጣቸው ናሙና መሰረት ለማሰራት ይፈልጋል፡፡
  • ሎት 4- አዳራሽ ሙሉ ዲኮር ወንበር በዲኮር ማልበስን እና መድረክ ብቻ ዲኮር እና በጨረታ ሰነዱ ዋጋ ዝርዝር ላይ የተገለፀውን ጨምሮ ለአንድ አመት ውል የሚቆይ፡፡
  • ሎት 5- የቅስቀሳ አገልግሎት ዲጄ፣ መድረክ መሪ ሙሉ ዘመናዊና ባህላዊ ባንድን እና የቅስቀሳ ሲቲ ባስን ተሽከርካሪን ጨምሮ ለአንድ አመት ውል የሚቆይ።

ስለሆነም በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተመለከቱትን መስፈርቶች በማሟላት መወዳደር ይችላሉ።

  1. በዘርፉ የታደሰ ሕጋዊ የንግድ ስራ ፈቃድ የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት፣ የግብር ከፋይ የምስክር ወረቀት፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ ስለመሆኑ ማረጋገጫ ሰርተፍኬት በጨረታ ላይ መካፈል የሚያስችል ክሊራንስ፣ በግዥ ኤጀንሲ ድረ ገጽ /online/ ተመዝጋቢ የሆኑ እና በጨረታ ሰነዱ ክፍል 3 ላይ በተቀመጠው ለእያንዳኑዱ ሎት ዝርዝር መመዘኛ የሚያሟላ መሆን አለበት።
  2. ተጫራቾች ከጨረታው መዝጊያ ቀንና ሰዓት ቀደም ብለው ናሙና የሚያስፈልጋቸውን ዕቃዎች ናሙናውን ለግዥ ቡድን ለተወከለው ባለሙያ ማስረከብ አለባቸው። ተጫራቾች የጨረታው ሰነድ በጨረታው ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ይመለስልን የማትሉት ለእያንዳንዱ ሎት ለየብቻ ብር 100.00 /አንድ መቶ ብር/ በመክፈል መግዛት ይኖርባቸዋል፡፡
  3. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ሎት1 ብር 20,000.00 /ሃያ ሺህ ብር/ ሎት2 ብር 10,000.00 /አስር ሺህ ብር/ ሎት3 ብር 5,000.00 /አምስት ሺህ ብር/፣ ሎት4 ብር 10,000.00 /አስር ሺህ ብርእና ሎት 5 ብር 10,000.00 /አስር ሺህ ብር/ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
  4. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ሲያሰሩ የሚያሰሩበት ስም ADDIS KETEMA SUBCITY ADMINISTRATION CHIEF EXECUTIVE PURCHASING ADMINISTARATION SUPPORITE PROCESS OFFICE በሚል ስም በማዘጋጀት በባንክ በተረጋገጠ ሲፒአ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  5. ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ባቀረቡት የመወዳደሪያ ሀሳብ ላይ ለውጥ ማድረግ እንዲሁም እራሳቸውን ማግለል አይችሉም፡፡
  6. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ከአንድ ሎት በላይ የተወዳደሩ ተወዳዳሪዎች እያንዳንዱን ሎት ለየብቻ የዋጋ ማቅረቢያውን ሙሉ ፍቃዳቸውን በፖስታ ኦርጅናል እና ኮፒ በማድረግ ከተሟላ ሰነድ ጋር ለየብቻ አያይዘው በማሸግ በፖስታው ላይ የተወዳደሩበትን ሎት እና ዘርፍ በጉልህ በሚታይ በመፃፍ ማቅረብ ይኖርባቸዋል። ካልፃፉ እና ለመለየት ከተቸገርን ፖስታውን ሳንከፍት ውድቅ እንደሚሆን ለማሳወቅ እንገደዳለን፡፡
  7. ተጫራቾች ከላይ የተጠቀሰውን ማስረጃዎች አሟልተው በሰም በታሸገ አንድ /1/ ኦርጂናል እና አንድ /1/ ኮፒ በማድረግ የዋና ስራ አስፈፃሚ /ቤት ግዥ ቡድን መድኃኒዓለም ከግሩም ሆስፒታል ከፍ ብሎ ባለው አስተዳደሩ /ቤት 7 ፎቅ ቢሮ ቁጥር 702 ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  8. አሸናፊ ተጫራች አሸናፊነቱ እንደተገለጸ የውል ማስከበሪያ 10% /../ ዋስትና በማስያዝ ውል መግባት ይኖርባቸዋል፡፡
  9. ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 11ኛው ቀን ከጠዋቱ 400 ሰዓት ተዘግቶ በዚያኑ ቀን ከጠዋቱ 415 ሰዓት ተጫራቾችን ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የዋና ስራ አስፈፃሚ /ቤት ግዥ ቡድን ቢሮ ላይ ይከፈታል። ሆኖም የመክፈቻ ቀኑ ቅዳሜ እና እሁድ ወይም የበዓል ቀን ከዋለ በሚቀጥለው የስራ ቀን ይሆናል፡፡ እንዲሁም ተጫራቹ በራሱ ምርጫ ጨረታው በሚከፈትበት ጊዜ ሳይገኝ ቢቀር ጨረታው መክፈት አያስተጓጉልም
  10. መስሪያ ቤቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ ለተጨማሪ መረጃ ስልክ ቁጥር 0118 69 38 76/0118 96 17 50 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡

አድራሻ - ከራስ ሃይሉ መዝናኛ ማዕከል አጠገብ አዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ህንፃ ዋና ስራ አስፈፃሚ ግዥ ቡድን 5 ፎቅ በግራ ክንፍ በኩል፡፡

 

በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ አስተዳደር የዋና ስራ አስፈፃሚ /ቤት ግዥ ቡድን

 

Save Tender