የጎንደር ከተማ አስተዳደር ገንዘብ መምሪያ አገልግሎት ለሚሰጣቸው ሴክተር መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን እቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የጎንደር ከተማ አስተዳደር ገንዘብ መምሪያ አገልግሎት ለሚሰጣቸው ሴክተር መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ
- በሎት 1. የጽህፈት መሳሪያ
- በሎት 2. የጽዳት እቃዎች
- በሎት 3. የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች
- በሎት 4. ቋሚ የቢሮ እቃዎች
- በሎት 5 የወታደሮች ከስክስ ቆዳ ጫማ ከ40 ቁጥር እስከ 43 ቁጥር
በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን እየገለፅን፣
ማቅረብ የምትችሉት መረጃ፡-
- የዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው
- የግብር መለያ ቁጥር /TIN/ ያላቸው
- የሚገዛው ግዥ የገንዘብ መጠን ከ200,000 /ከሁለት መቶ ሺህ/ ብርና ከዛን በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ መሆን ይኖርበታል፡፡
- ተጫራቾች ከላይ ከተራ ቁጥር 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ከሎት 1 እስከ ሎት 5 የሚገሳን እቃ ዝርዝር መግለጫ /ስፔስፊኬሽን/ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ / ቢድ ቦንድ/ ከሚያቀርቡት ጠቅላላ ዋጋ ላይ 1% በባንክ የተረጋገጠ የክፍያ ትእዛዝ /ሲ.ፒ.ኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 100 /መቶ ብር/ በመክፈል ጎን ከተማ አስ/ገንዘብ መምሪያ ቢሮ ቁጥር 11 መውሰድ ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የመጫረቻ ሃሳባቸውን አንድ ወጥ በሆኑ ዋናና ቅጅ በማለት በጥንቃቄ በመሙላት በታሸገ ፖስታ ጎን/ከ/አስ/ግዥና/ንብ/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 5 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ዘወትር በስራ ሰዓት ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ዋጋውን በሚሞሉበት ወቅት ስርዝ ድልዝ መኖር የለበትም፡፡
- ተጫራቾች በሚያቀርቡት የመወዳደሪያ ሃሳብ ላይ ሙሉ ስምና ፊርማቸውን የድርጅቱን ማህተም ማድረግ አለባቸው፡፡
- ጨረታው በአየር ላይ የሚቆይበት ጊዜ ይህ ጨረታ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት በጎንደር ከ/አስ/ገንዘብ መምሪያ ቢሮ ቁጥር 11 በመምጣት የጨረታ ሰነድ መግዛት ይችላሉ፡፡ ጨረታው በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ታሽጎ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ባይገኙም ጨረታው ይከፈታል፡፡ የሚከፈትበት ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን የሚከፈት ይሆናል፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የሚቀርበው ቅሬታ ካለ ጨረታው ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 5 የስራ ቀናት ማቅረብ የሚችሉ ሲሆን ከ5 የስራ ቀናት በኋላ የሚቀርብ ቅሬታ የማንቀበል መሆኑን እንገልጻለን፡፡
- ለተጨማሪ መረጃ ካስፈለገ ጎን/ከተ/አስ/ገንዘብ መምሪያ ቢሮ ቁጥር 5 በአካል በመምጣት ወይም በስልክ ቁጥር 058 126 03 06 ደውሎ መጠየቅ ይችላሉ፡፡
- የሚገዛውን እቃ ጎን/ከ/አስ/ገንዘብ መምሪያ ድረስ በራሱ ትራንስፖርት ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
- ተጫራቾች መጫረት /መወዳደር/ የሚችሉት የንግድ ዘርፍ በሚመለከታቸው ይሆናል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ማሳሰቢያ፡- አሸናፊው ተጫራች የሚያቀርበው እቃ ኦርጅናልና በወጣው እስፔስፊኬሽን እንዲሁም በምናቀርበው ናሙና መሰረት ይሆናል፡፡ የሚፈጸመው ግዥ ከበጀት አንጻር ሊቀንስ ወይም ሊጨምር የሚችል መሆኑን፡፡ አሸናፊው የሚለየው በያንዳንዱ ሎት ጠቅላላ ዋጋ ይሆናል፡፡ ከተዘረዘሩት እቃዎች ውስጥ አንዱን ያልሞላ ከውድድር ውጪ ይሆናል፡፡
በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የጎንደር ከተማ አስተዳደር ገንዘብ መምሪያ
