በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አታቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ የወረዳ 6 ፋይናንስ ጽ/ቤት ከዚህ በታች በሎት የተዘረዘሩትን እቃዎችና አገልግሎቶች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
የጨረታ ማስታወቂያ
የግዥ መለያ ቁጥር 02/18
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አታቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ የወረዳ 6 ፋይናንስ ጽ/ቤት ከዚህ በታች በሎት የተዘረዘሩትን እቃዎችና አገልግሎቶች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
- ሎት-1፣ የደንብ ልብስ
- ሎት-2፣ የፅዳት ዕቃዎች
- ሎት-3፣ ቋሚ የቢሮ እቃዎች
- ሎት-4፣ መስተንግዶ
- ሎት-5፣ ትራንስፖርት/የመኪና ኪራይ አገልግሎት
ስለሆነም በጨረታው መሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች ማሟላት የሚገባቸው ቅድመ ሁኔታዎች
- የዘመኑ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው::
- የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆናቸውን የሚገልፅ የምስክር ወረቀት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (Tin) የተመዘገቡበትን ሰርተፍኬት ማቅረብ አለባቸው።
- የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ መሆናቸውን ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- በአቅራቢዎች ስም ዝርዝር የተመዘገቡበትን መረጃ ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO) 2% በአቃ/ቃ/ክ/ከ/ወረዳ 6 ፋይናንስ ጽ/ቤት በሚል ስም አሰርቶ ከሰነዱ ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- የተዘረዘሩትን ዕቃዎች ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ 200 ብር (ሁለት መቶ ብር) በመግዛት በአቃ/ቃ/ከ/ከ/ወረዳ 6 ፋ/ጽ/ቤት ቢሮ 3ኛ ፎቅ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 10 ተከታተይ የሥራ ቀን በአየር ላይ ቆይቶ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ጨረታው ታሽጎ 11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ተጫራቾች (ሕጋዊ ወኪሎቻቸው) በተገኙበት የሚከፈተው ሲሆን ቀኑ የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይሆናል፡፡
- የጨረታ ሰነዱ በታሸገ ኤንቨሎፕ በማሸግ ለጨረታው በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ የገዙትን የጨረታ ሰነድ ሙሉውን ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የውል ማስከብሪያ 10% በባንክ በተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ (CPO) በአቃ/ቃ/ክ/ከ/ወረዳ 6 ፋይናንስ ጽ/ቤት በሚል ስም አሰርቶ ከሰነዱ ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ኮፒ በማድረግ ኦርጅናልና ኮፒ ብሎ በመለየት በጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርበታል፡፡
- ናሙና ለሚያስፈልጋቸው ዕቃዎች ጨረታው ከመከፈቱ ከ1 ቀን በፊት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፤ ዝርዝርስፔሲፊኬሽን ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- የሚሞላው ዋጋ ቫትን ያካተተ መሆን አለበት፡፡
- ተቋሙ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ፡- አቃ/ቃ/ክ/ከተማ ወረዳ 6 አስተዳደር ጽ/ቤት
ሳሪስ- ከሬስ ኢንጂነሪነግ ከፍ ብሎ
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ የወረዳ 6 ፋይናንስ ጽ/ቤት
