በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በጤና ጥበቃ ቢሮ የደብረሲና የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል በ2018 በጀት አመት ለሚፈፅማቸው ግዥዎች ማለትም ሎት 1. የፅህፈት መሳሪያ ግዥ፣ ሎት 2 ጽዳት እቃዎች ግዥ፣ ሎት 3 የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች ግዥ፣ ሎት 4. የመኪና ጎማ ግዥ እና ሎት 5. የህትመት ግዥ ለመፈፀም በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 03/2018
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በጤና ጥበቃ ቢሮ የደብረሲና የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል በ2018 በጀት አመት ለሚፈፅማቸው ግዥዎች ማለትም ሎት 1. የፅህፈት መሳሪያ ግዥ፣ ሎት 2 ጽዳት እቃዎች ግዥ፣ ሎት 3 የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች ግዥ፣ ሎት 4. የመኪና ጎማ ግዥ እና ሎት 5. የህትመት ግዥ ለመፈፀም በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ በዚህም መሰረት፡-
1. በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ማቅረብ የሚችል፤
2. የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር /TIN/ ያላቸውና ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣
3. የሚሞሉት ጠቅላላ ዋጋ ከብር 200,000.00 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ እና በላይ ከሆነ የቫት ተመዝጋቢነት ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣
4. የጨረታ ሰነዱን ብር 150.00 /አንድ መቶ ሃምሳ ብር/ በመክፈል ከሆስፒታሉ ግዥ ፋይ/ንብ/አስ/ደ/የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 62 መውሰድ ይችላሉ፡፡
5. የጨረታ ማስከበሪያ ያስገቡትን ጠቅላላ ዋጋ 2% ያከሉን ለሆስፒታሉ በCPO /በጥሬ ገንዘብ/ ማስያዝ አለባቸው።
6. ከብር 20,000.00 /ሃያ ሺህ ብር/ በላይ ለሚዝዙ እቃዎችና ከብር 10,000.00 /አስር ሺህ ብር አገልግሎቶች 3% የመቁረጥ ግዴታ አለብዎት፡፡
7. ለሁሉም ሎቶች የሚያቀርቡት ሰነድ ላይ መሉ አድራሻቸውን፣ ስማቸውን፣ ፊርማቸውን እና የድርጅታቸውን ማህተም ማስቀመጥ አለባቸው።
8. የሁለቱም ጨረታዎች አሸናፊ ሆኖ የተመረጠው ድርጅት አሸናፊነቱ ከተገለፀለት ከ5 የስራ ቀናት በኋላ ባሉት 5 ቀናት ውስጥ የውል ማስከበሪያ 10% ያሸነፉበትን ጠቅላላ ዋጋ በCPO በጥሬ ገንዘብ በማስያዝ ውል መውሰድ የሚችል መሆን ይኖርበታል፡፡
9. ተጫራቾች የሚያቀርቡትን ነጠላ ዋጋና ጠቅላላ ዋጋ ዝርዝር አባሪ ዶክሜንቶችን ጨምሮ የጨረታ ሰነዱን ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ በፖስታ አሽገው ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
10. ጨረታው ክፍት ሆኖ የሚቆየው ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት ክፍት ሆኖ ይቆይና በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት የጨረታ ሳጥኑ ይታሸጋል፡፡
11. ጨረታው በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡30 ሰዓት ላይ በሆስፒታሉ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ተጫራቾች ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የሚከፈት ሲሆን ተጫራቾች ባይገኙም ጨረታው የሚከፈት ይሆናል፡፡
12. ለሁሉም ሎቶች ተጨማሪ መረጃዎችን ከጨረታው መመሪያና ከዋጋ መሙያ ላይ ማየት ይቻላል፡፡
13. ጨረታው የሚከፈትበት ቀን የመንግስት የስራ ቀን ካልሆነ ዝግ ከሆነ በቀጣይ ባለው የስራ ቀን ይከፈታል።
14. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
15. ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 0913869679፣ 0925402088 ወይም 0924854239 ደውለው ይጠይቁ
አድራሻ፡-
ከአዲስ አበባ ወደ ደሴ በሚወስደው ዋና መንገድ ላይ 190 ኪሎ ሜትር ደብረሲና ከተማ
የደብረሲና የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል
