የሀዋሳ ከተማ አስ/ፋ/መምሪያ ለሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ለ23ቱም ሴክተር መስሪያ ቤቶች በ2018 በጀት ዓመት በታቀደው መሰረት የህትመትና የፈርኒቸር ግዥ ለመፈጸም በግልጽ ጨረታ በማወዳደር በዘርፉ ፈቃድ ካላቸው አቅራቢዎች መካከል በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
የጨረታ ማስታወቂያ
የሀዋሳ ከተማ አስ/ፋ/መምሪያ ለሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ለ23ቱም ሴክተር መስሪያ ቤቶች በ2018 በጀት ዓመት በታቀደው መሰረት የህትመትና የፈርኒቸር ግዥ ለመፈጸም በግልጽ ጨረታ በማወዳደር በዘርፉ ፈቃድ ካላቸው አቅራቢዎች መካከል በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
በዚህ መሠረት፤-
1) ፈርኒቸር ዕቃዎች ግዥ ሎት 01/2018
2) የህትመት ግዥ ሎት 02/2018
ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ አቅራቢዎች መወዳደር ይችላሉ፡-
1. በሥራ መስኩ ህጋዊ የታደሰ ንግድ ፍቃድ፣
2. የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉና የዘመኑን ግብር መክፈላቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ ፣
3. ተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ የሆኑ፣
4. የአቅራቢነት ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው፣
5. ከሚመለከተው መ/ቤት የታክስ ክሊራንስ ማቅረብ አለበት፤
6. የጨረታ ሰነዱን ከሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ መምሪያ ቢሮ (አዲሱ ከተማ አስተዳደር ህንፃ) አራተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 54 (ሃምሳ አራት) በመቅረብ ይህ ጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 /ለአሥር/ ተከታታይ ቀናት ውስጥ ቀርባችሁ ሰነድ ብር 500 (አምስት መቶ ብር) በመክፈል መግዛት ይችላሉ፡፡
7. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ በየሎቱ ብር 100,000 (አንድ መቶ ሺህ ብር) በባንክ የተረጋገጠ (የተመሰከረ) ሲ ፒ ኦ (CPO) ወይም ቢድ ቦንድ ከጨረታ ሰነድ ጋር ማቅረብ አለባቸው፡፡
8. ጨረታ ሰነዱ በሰም ለየብቻቸው በታሸገ ኤንቬሎፕ አንድ ኦርጂናል እና ሁለት ኮፒ ፋይናንሻል በመያዝ በማሽን ተወዳዳሪዎች ቴክኒክ ሰነድ ጭምር በመያዝ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 10 (አሥር) ተከታታይ ቀናት ፋይናንስ መምሪያ ቢሮ ቁጥር 54 (ግዥ ኬዝ ቲም) ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
9. ጨረታው በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡30 ሰዓት ታሽጎ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበትም ሆነ ባልተገኙበት ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት በቢሮ ቁጥር 54 ይከፈታል፡፡ ይህ ቀን በበዓላት ፤ቅዳሜ ወይም እሁድ ከሆነ ቀጥሎ ባለው የሥራ ቀን በተመሣሣይ ሠዓት የሚታሸግና የሚከፈት ይሆናል፡፡
10. መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ስልክ ቁጥር 046-212-13-34
የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስና ኢኮ/ል/መምሪያ
