የኢትዮጵያ ልማት ባንክ አዳማ ዲስትሪክት ለኬኛ ጠቅላላ የንግድ ሥራ ኃ/የተ/የግ/ማህበር እና ለእንዳልካቸው ንጋቱ ለሰጠው ብድር አመላለስ በመያዣነት የያዛቸውን እና ከዚህ በታች በሰንጠረዥ የተገለፁትን ፕሮጀክቶች እና የመያዣ ንብረቶቹን በአዋጅ ቁጥር 97/90 በተሻሻለው 216/92 እና 1147/2011 መሰረት ባሉበት ሁኔታ በዝግ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።
የዝግ ጨረታ ሽያጭ ማስታወቂያ
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ አዳማ ዲስትሪክት ለኬኛ ጠቅላላ የንግድ ሥራ ኃ/የተ/የግ/ማህበር እና ለእንዳልካቸው ንጋቱ ለሰጠው ብድር አመላለስ በመያዣነት የያዛቸውን እና ከዚህ በታች በሰንጠረዥ የተገለፁትን ፕሮጀክቶች እና የመያዣ ንብረቶቹን በአዋጅ ቁጥር 97/90 በተሻሻለው 216/92 እና 1147/2011 መሰረት ባሉበት ሁኔታ በዝግ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።
|
ተ.ቁ |
ተበዳሪው/የመያዣ ሰጪው/ ስም |
የሚሸጠው ንብረትና የሚገኝበት ቦታ |
የጨረታው መነሻ ዋጋ |
ደረጃ |
ጨረታው የሚካሄድበት ቦታ፣ ቀን እና ሰዓት |
|
1. |
ኬኛ ጠቅላላ የንግድ ሥራ ኃ/የተ/የግ/ማህበር |
በኦሮሚያ ብ/ክ/መንግስት በአርሲ ዞን ዶዶታ ወረዳ፣ አዋሽ ብሾላ ቀበሌ ውስጥ 1 ሄክታር ይዞታ ላይ ያረፉ ግንባታዎች፣ የእንሰሳ (በግ/ፍየል) ማረጃ ማሽኖች፣ ጀኔሬተር እና አንድ ባለ ማቀዝቀዣ ዩዲ ኒሳን ተሽከርካሪ |
44,999,333.61 |
2ኛ |
በኢትዮጵያ ልማት ባንክ አዳማ ዲስትሪክት መ/ቤት የካቲት 05 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት |
|
2. |
እንዳልካቸው ንጋቱ |
በኦሮሚያ ብ/ክ/መንግስት በምስራቅ ሸዋ ዞን ሎሜ ወረዳ፣ ጆጎ ጉዴዶ ቀበሌ ውስጥ 6000 ካ.ሜ ይዞታ ላይ ላይ ያረፉ - ግንባታዎች የወተት ማቀነባበሪያ ማሽኖች እና 6(ስድስት) ተሽከርካሪዎች |
46,286,021.48 |
2ኛ |
በኢትዮጵያ ልማት ባንክ አዳማ ዲስትሪክት መ/ቤት የካቲት 06 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት |
ማሳሰቢያ፡-
1. ተጫራቾች የጨረታውን መነሻ ዋጋ 25% (ሃያ አምስት በመቶ) የባንክ ክፍያ ማዘዣ (ሲፒኦ) ብቻ በማስያዝ መጫረት ይችላሉ፡፡
2. ተጫራቾች የሚገዙትን ንብረት፤ የሚገዙበትን ዋጋ፤ ስምና አድራሻ በመጥቀስ ሌሎች አስፈላጊ የሆኑ መረጃዎችን በማያያዝ በኢትዮጵያ ልማት ባንክ አዳማ ዲስትሪክት መ/ቤት ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለጨረታ ተ.ቁ 1 እስከ የካቲት 05 ቀን 2018 ዓ.ም 3:30 ሰዓት ድረስ ማስገባት ያለባቸው ሲሆን ለጨረታ ተ.ቁ 2 እስከ የካቲት 06 ቀን 2018 ዓ.ም 3፡30 ሰዓት ድረስ ማስገባት አለባቸው፡፡
3. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ከኢትዮጵያ ልማት ባንክ አዳማ ዲስትሪክት መውሰድ ይችላሉ፡፡
4. ንብረቶቹን በብድር መግዛት የሚፈልግ ተጫራች የባንኩን የብድር መስፈርት ማሟላትና ንብረቱን የሚገዙበት ዋጋ፣ ስለ ቀሪው የንብረት ዋጋ አከፋፈል ሁኔታ፣ ለቀሪው የንብረት ዋጋ አከፋፈል ከሚገዙት ንብረት በተጨማሪ የሚያቀርቡት የመያዣ ዓይነት ግምትና የሚገኝበት ቦታ በመጥቀስ በታሸገ ፖስታ ማስገባት ይኖርበታል፡፡
5. አሸናፊው ያስያዘውን ገንዘብ ከግዢው ዋጋ ሲታሰብለት ለተሸነፉ ተጫራቾች ያስያዙትን ሲፒኦ ተመላሽ ይደረጋል፡፡
6. የጉምሩክ ቀረጥና ታክስ ያልተከፈለባቸው የፕሮጀክቱ ንብረቶች ካሉ ገዢው የቀረጥ ነጻ መበት ሊኖረው አሊያም በመንግስት የሚፈለገውን ቀረጥ ለመክፈል ይገደዳል።
7. የጨረታው አሸናፊ 15% የተጨማሪ እሴት ታክስ /VAT/ ጨምሮ ሌሎች ገዢ እንዲከፍላቸው በሕግ የተወሰነ ክፍያዎችን እንዲሁም የስም ማዛወሪያ ክፍያን ጨምሮ ገዢው ይከፍላል፡፡
8. ባንኩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
9. ዝርዝርና ተጨማሪ መረጃ በተመለከተ የኢትዮጵያ ልማት ባንከ አዳማ ዲስትሪክት መስሪያ ቤት በአካል በመቅረብ ማነጋገር እና ንብረቱን መጎብኘት የሚፈልግ ተጫራች ከዲስትሪከቱ ጋር አስቀድሞ ቀጠሮ በማስያዝ መጎብኘት ይችላሉ፡፡
ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር 022-211-66-87 ላይ መደወል ይቻላሉ፡፡
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ አዳማ ዲስትሪክት
