በኢትዮ ኢንጅነሪንግ ግሩፕ አዳማ የግብርና ማሽነሪ ማምረቻ ኢንዲዱስትሪ ለ2018 በጀት ዓመት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ለሰራተኛ ለስራ አገልግሎት የሚውሉ የስቴሽነሪ ዕቃዎች፣ የክበብ (የካፌ አገልግሎትና የተለያዩ የትራክተርና የፓምፕ ጎማዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
የግዢ ጨረታ ማስታወቂያ
በኢትዮ ኢንጅነሪንግ ግሩፕ አዳማ የግብርና ማሽነሪ ማምረቻ ኢንዲዱስትሪ ለ2018 በጀት ዓመት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ለሰራተኛ ለስራ አገልግሎት የሚውሉ የስቴሽነሪ ዕቃዎች፣ የክበብ (የካፌ አገልግሎትና የተለያዩ የትራክተርና የፓምፕ ጎማዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
· ሎት1 የስቴሽነሪ ዕቃዎች
· ሎት2 የካፌ አገልግሎት ግዥ
· ሎት3: የተለያዩ የትራክተርና
የፓምፕ ጎማዎች
· በመሆኑም በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 10 የስራ ቀናት ያህል ሰነዱን አዳማ የግብርና ማሽነሪ ማምረቻ ኢንዱስትሪ በግዥ ከፍል ቢሮ ቁጥር 014 በመገኘት መውሰድ (መግዛት) ይችላሉ፡፡
· ተጫራቾች ከሚያቀርቡት እቃ ጋር ተዛማጅ የሆነ በዘመኑ የታደሰ ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ፣ የምዝገባ የምስክር ወረቀት ማስረጃ ማቅረብ የሚችል፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ የምስክር ወረቀት የዘመኑን ግብር የከፈሉ፤ የቫት ተመዝጋቢነት ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ እንዲሁም የግብር ክሊራንስ /ጨረታ ለመሳተፍ የሚሰጥ/ የሚያስችል ምዝገባ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው።
· ተወዳዳሪዎች በጨረታው ላቀረቡት ዕቃ ወይም አገልግሎት በጨረታ መመሪያው የተገለጸውን የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ማቅረብ አለባቸው። የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በተጫራቹ ምርጫ ከሚከተሉት ዓይነቶች አንዱ ሊሆን ይችላል፡፡
(ሀ) በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና፣
(ለ) በጥሬ ገንዘብ ወይም የክፍያ ትዕዛዝ /CPO/ የባንክ ጋራንቲው 60 ቀንና ከዚያ በላይ መሆን አለበት፣
· ተጫራቾች ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 10 (የስራ ቀናት በአዳማ የግብርና ማሽነሪ ማምረቻ ኢንዱስትሪ በግዢ ክፍል ቢሮ ቁጥር 014 በመገኘት ሰነዱን በጨረታ ሰነዱ ውስጥ በተገለፀው አስተሻሸግ መሰረት ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡
· ጨረታው የጨረታው ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 10 ስራ ቀናትን አልፎ በ11ኛው ቀን ከረፋዱ 8፡00 ሰዓት ተዘግቶ በእለቱ ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ተጫራቾች /ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከታች በተገለፀው አድራሻ በአዳማ የግብርና ማሽነሪ ማምረቻ ኢንዱስትሪ የስብሰባ አዳራሽ ጨረታው ይከፈታል ቀኑ የበዓል ወይም የእረፍት ቀን ከሆነ በቀጣዩ የስራ ቀን ከላይ በተገለፀው ሰዓት ይከፈታል፡፡ የተጫራች አለመኖር ፖስታው ተሟልቶ እስከተገኘ ድረስ ጨረታውን ለመከፈት አያስተጓጉልም፡፡
· ኢንዱስትሪው የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
· የካፌ አገልግሎት ግዥን በተመለከተ አጠቃላይ የሚያስፈልጉ የመብራት፣ የውሃ፣ የኤሌክትሪክና የማብሰያ ዕቃዎች የመሳሰሉትን በኢንዱስትሪው በኩል የሚሸፈን ይሆናል፡፡
· ተጨማሪ ማብራሪያ ካስፈለገ በአካል በመቅረብ ወይም በስልክ ቁጥር 0221110689/0912264680 ደውሎ መጠየቅ ይችላሉ፡፡
አድራሻ፡- አዳማ ከወንጂ ማዞሪያ ተቃራኒ አቅጣጫ 500 ሜ ላይ
ስልክ:- 0221110689/09122646804- ፋክስ:-0221111866
በኢትዮ-ኢንጅነሪንግ ግሩኘ አዳማ የግብርና ማሽነሪ ማምረቻ ኢንዱስትሪ
