የኢትዮጵያ የኢንዱስትሪ ግብዓቶች ልማት ድርጅት የትራንስፖርት አገልግሎት በጨረታ አወዳድሮ አገልግሎቱን ለመግዛት ይፈልጋል።
ኤግልድ
የኢትዮጵያ የኢንዱስትሪ ግብዓቶች ልማት ድርጅት የትራንስፖርት አገልግሎት ግዥ ጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 05/18
ድርጅታችን የገዛውን ፓልም የምግብ ዘይት፣ ሸቀጣ ሸቀጥ፣ ስኳር፣ ሲሚንቶ እና የኢንዱስትሪ ጨዉ መነሻዉን የፓልም የምግብ ዘይት ከእንዶዴ እና ከጅቡቲ፣ ሸቀጣ ሽቀጥ አ/አበባ ከሚገኘዉ የደርጅቱ መጋዘኖች፣ ለስኳር ከሁሉም የስኳር ኢንዱስትሪ ፋብሪካዎች እና አ/አበባ ከሚገኘው መጋዘኖቹ፣ ስሚንቶ ከሁሉም የሲሚንቶ ፋብሪካዎች እና የኢንዱስትሪ ጨው ከሱማሌ ክልል አፍዴራ ዞን ሀርገሌ ዩኦ ጨው አቅራቢ ማህበራት እና ከአፋር ክልል አፍዴራ ጨው አቅራቢ ማህበራት ለተለያዩ በክልል ወደ ሚገኙት የድርጅቱ ቅ/ፎች ለማጓጓዝ በግልፅ ጨረታ የትራንስፖርት አገልግሎት አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለሆነም በጨረታው መካፈል የሚፈልጉ ከዚህ በታች የተመለከቱትን መስፈርቶቹን የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታው መካፈል የሚችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
1. በዘርፉ የታደሰ የንግደ ሥራ ፈቃድ፣ የብቃት ማረጋገጫ፣ ታክስ ክሊራንስ ሠረተፍኬት እና የግብር ከፋይነት ምዝገባ ሠረተፍኬት ያላቸው መሆን ይገባቸዋል፡፡
2. ተጫራቾች ለጨረታው የተዘጋጀውን ዝርዝር የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል ፒያሳ ቢስ መብራት አካባቢ /አትክልት ተራ/ ከሚገኘው የድርጅቱ ዋና መስርያ ቤት ከሎጀስቲክስ ዳይሬክቶሬት ቢሮ በመቅረብ መውሰድ ይችላሉ፡፡
3. ተጫራቾች ለፓልም የምግብ ዘይት ማጓጓዝ የጨረታ ማስከበሪያ ብር 300,000.00 (ሰስት መቶ ሺ ብር)፣ ለሸቀጣ ሸቀጥ ብር 100,000.00 (አንድ መቶ ሺ ብር)፣ ለስኳር ተጫራቾች ብር 100,000 (አንድ መቶ ሺ)፣ ለሲሚንቶ ተጫራቾች ብር 100,000 (አንድ መቶ ሺ) እና ለኢንዱስትሪ ጨው ብር 200,000 (ሁለት መቶ ሺ) በባንክ በተመሰከረ የክፍያ ትዕዛዝ (CPO) ብቻ ከትራንስፖርት ታሪፍና ከብቃት ማረጋገጫ ማስረጃዎች ጋር ያይዞ መቅረብ ይኖርበታል፡፡
4. የጨረታ መወዳደሪያ ዋጋቸውንና ከላይ የተጠቀሱ ህጋዊ ሰነዶችን በታሸገ ኤንቨሎፕ አንድ ኦርጅናል እንዲሁም አንድ ኮፒ በማድረግ እና በአንድ ፖስታ በማሸግ ጥር 18 ቀን 2018 ዓ.ም ከረፋዱ 4፡00 ሰዓት ድረስ ማቅረብ ይጠበቅባችዋል፡፡
5. ጨረታው ጥር 18 ቀን 2018 ዓ.ም ከረፋዱ 4፡10 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
6. ተጫራቾች በጨረታው መመሪያ ላይ የተገለፀውን ደንብና ግዴታ በሙሉ የመፈፀም ግዴታ አለባቸው።
ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
የኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ግብዓቶች ልማት ድርጅት
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 011-126-22-50
