ድርጅታችን ኢትዮጵያን ሴንተር ፎር ዴቨሎፕመንት /ECD/ ለነዚህ በፐሮጀክቱ ለታቀፉ ቅድመ አንደኛ ትምህርት ቤቶች አገልግሎት የሚሆኑ የተለያዩ ግብዓቶችን ለመግዛት አቅዷል፡፡ በመሆኑም የሚከተሉትን ቁሳቁሶች ለማቅረብ የምትፈልጉ እና መስፈርቶቹን የምታሟሉ አቅራቢዎች በጨረታው መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡
የጨረታ ማስታወቂያ
ኢትዮጵያን ሴንተር ፎር ዴቨሎፕመንት /ECD/ ከ ችልደርን ኢን ከሮሰፋዬር /CiC/ በጋራ በመሆን በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሥር በሚገኙ 9 የ ቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ላይ"Pathway to learning an integrated school Readiness Program for early learners" የሚል ፕሮጀከት በመተግበር ላይ ይገኛሉ፡፡ በመሆኑም ድርጅታችን ኢትዮጵያን ሴንተር ፎር ዴቨሎፕመንት /ECD/ ለነዚህ በፐሮጀክቱ ለታቀፉ ቅድመ አንደኛ ትምህርት ቤቶች አገልግሎት የሚሆኑ የተለያዩ ግብዓቶችን ለመግዛት አቅዷል፡፡ በመሆኑም የሚከተሉትን ቁሳቁሶች ለማቅረብ የምትፈልጉ እና መስፈርቶቹን የምታሟሉ አቅራቢዎች በጨረታው መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡
የሚገዙት ቁሳቁሶችም የሚከተሉት ናቸው፡፡
* ሎት 1 ለህፃናት መዋያ /Day care center/ አገልግሎት የሚሆኑ የተለያዩ ቁሳቁሶች
* ሎት 2 የከፍል ውጭ መጫዎቻ /outdoor playing equipment's/ መሳሪያዎች ተጫራቾች ማሟላት ያለባቸው መስፈርቶች
1. ለዘመኑ የታደሰ የንግድ ፍቃድ ማቅረብ የሚችሉ፣
2. የቲን ምዝገባ ሰርተፊኬቱን ማቅረብ የሚችሉ፣
3.የቫት ተመዝጋቢ የሆኑ እና ሰርተፊኬቱን ማቅረብ የሚችሉ፣
4. ቁሳቁሶቹን በተቀመጠው ስፔሲፊኬሽን መሠረት ማቅረብ የሚችሉ፣
5. ያሸነፉበትን እቃዎች በራሳቸው ትራንስፖርት አጓጉዘው ድርጅቱ ወደሚያዘጋጀው ስቶር ማድረስ የሚችሉ፣
ከላይ የተጠቀሱትን መስፈርቶች የምታሟሉ ሕጋዊ ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 5 ተከታታይ የሥራ ቀናት ከድርጅታችን የጨረታ ሰነዱን በነጻ በመውሰድ ቁሳቁሶቹን የምታቀርቡበትን ዋጋ በታሸገ ኤንቨሎፕ ማስገባትና መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡
አድራሻ፡- ኢትዮጵያን ሴንተር ፎር ዴቨሎፕመንት /ECD/አዲስ አበባ፣ ቦሌ ዓለም ሕንፃ 7ኛ ፎቅ
ስልክ:- 098288 2826
ማሳሰቢያ፦
1. አሸናፊ ተጫራቾች ያሸነፉበትን ግብዓት ከማቅረባቸው በፊት ሳምፕል ማሳየት ይኖርባችኋል።
2. ተጫራቾች የምታቀርቡት ዋጋ ቫትን ያካተተ መሆን አለመሆኑን በግልጽ ማሳየት ይኖርባችኋል፡፡ በትከክል ካልተገለጸ ቫት እንደተካተተ ተደርጎ ይቆጠራል፡፡
3. ድርጅታችን የተሻለ አማራጭ ካገኘ ያለ ምንም ቅድመ ማስጠንቀቂያ እና ማስታወቂያ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ኢትዮጵያን ሴንተር ፎር ዴቨሎፕመንት /ECD/
