የዲላ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በ2018 ዓ/ም የበጀት ዘመን ለትምህርት ስልጠና የሚውሉ ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
የዕቃ ግዥ የጨረታ ማስታወቂያ
የዲላ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በ2018 ዓ/ም የበጀት ዘመን ለትምህርት ስልጠና የሚውሉ ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
በመሆኑም ዕቃዎች የሚገዛላቸዉ የትምህርት ክፍሎች ፡-
1. አኒማል ፕሮዳክሽን
2. አውቶ መካኒክስ ዲ/ት
3. ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጅ ዲ/ት
4. ብዩልድንግ ኤሌክትሪካል ኢንስታሌሽን
5. ኤሌክትሪካል ኤሌክትሮኒክስ ዲ/ት
6. ጋርመንት ዲ/ት
7. የእንጨት ሥራ ዲ/ት
8. ማንፋክቸሪንግ ዲ/ት
9. ሆቴል ዲ/ት
10. የጽ/መሳርያዎች እና የጽዳት ዕቃዎች
በመሆኑም ከላይ ለተዘረዘሩ የሥልጠና ዘርፎች እና የጽህፈት መሳርያዎችና የጽዳት ዕቃዎች ለመወዳደር የሚትፈልጉ ተወዳዳሪዎች /አቅራቢዎች ከዚህ በታች የተዘረዘተሩትን መስፈርት ማሟላት ይጠበቅባቸዋል፡፡
1. የጨረታው ተወዳደሪ /አቅራቢ/ ድርጅት የ2018 ዓ/ም የታደሰ የንግድ ፍቃድ ማቅረብ የሚችል መሆን ይጠበቅበታል፡፡
2. የገንዘብና ኢኮ/ል/ሚኒስተር ባዘጋጀው የዕቃ አቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው።
3. ተጫራቾች የተጨማር እሴት ታክስ /ቫት/ ተመዝጋቢ መሆናቸውን የማረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው።
4. ተጫራቾች የተዘረዘሩትን ዕቃዎች ናሙና ማቅረብ የሚችሉና ቋሚ ዕቃዎችን ገዥው መ/ቤት በአካል ቀርቦ ለማየት ከፈለጉ ለመተባበር ፍቃደኛ ሊሆኑ የሚችሉ መሆን አለባቸው።
5. ተጫራቾች የዋጋ ዝርዝራቸውን በገዙት የጨረታ ሰነድ ላይ ብቻ ሞልተው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
6. ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት ዕቃ ዋጋው ከቫት ውጭና ከነቫቱ ጋር ተብሎ በጥራት መሞላት ይኖርበታል፡፡ እንድሁም ቫት ከተካተተበት ተካቶበታል ተብሎ እንድሁም ያልተካተተ ከሆነ አልተካተተም ተብሎ ሊጸፍ ይገባዋል፡፡ ይህ ሳይሆን ቢቀር ቫት እንደተካተተ አድርጎ መ/ቤቱ የሚወስድ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
7. ተጫራቾች የሚጫረቱበትን የጠቅላላ ዋጋ 2% ብር 10,000.00 የጨረታ ማስከበሪያውን በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማስገባት አለባቸው።
8. ጨረታውን ያሸነፈ ተጫራች ከፖሊ ኮሌጁ ጋር ውል ተዋውሎ የውል ማስከበሪያ የጠቅላላ ዋጋውን 10% ማስያዝ ይኖርበታል፡፡ በተጨማር ያሸነፈበትን ዕቃ በ15 ቀናት ውስጥ ለኮሌጁ የማቅረብ ግዴታ አለበት፡፡ ይህ ሳይሆን ቢቀር ለጨረታ ማስከበርያ ያስያዙት 10 % ገንዘብ በቀጥታ ለፖሊ ኮሌጁ ገቢ ሆኖ ከጨረታው የሚሰረዙ ይሆናል፡፡
9. የጨረታ ዶክመንቱን ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን አንስቶ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት ከኮሌጁ ግዥና ንብረት አስተዳደር ብሮ ቁጥር 4 በመቅረብ የማይመለስ ብር 100.00 /አንድ መቶ/ ብር በኮሌጁ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በአካውንት ቁጥር GOV 1000019294718 ዲላ ፖሊ ቴ/ኮሌጅ በማለት እና በማስገባትና አድቫይስ በማቅረብ የጨረጋ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡
10. ተጫራቾች የሚያቀርቡትን የመወዳደሪያ ሰነድ ዋናውንና ፎቶ ኮፒውን ለየብቻ ማህተም አሳርፎበት በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
11. ጨረታው በ16ው ቀን ከጠዋቱ 3፡30 ታሽጎ ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፣ 16ኛው ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ የጨረታ ሰነዱ በሚቀጥለው ቀን በተመሳሳይ ሰዓት የሚገባና የሚከፈት ይሆናል፡፡ በተጫራች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባለመገኘታቸው የጨረታውን አከፋፈት አያስተጓጉለውም።
12. ኮሌጁ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፍል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 0463312716 ወይም 0463312719 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል::
ዲላ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ
