አዲስ አበባ የከተማ አውቶቡስ አገልግሎት ድርጅት ለተለያዩ አገልግሎት የሚውሉ ክፍሎች /ቦታዎችን/ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ማከራየት ይፈልጋል፡፡
ግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር አአከአአድ/ሱኪኪጨቁ/…/001/2018
አዲስ አበባ የከተማ አውቶቡስ አገልግሎት ድርጅት ለተለያዩ አገልግሎት የሚውሉ ክፍሎች /ቦታዎችን/ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ማከራየት ይፈልጋል፡፡
ስለሆነም፣ በጨረታው ላይ መሳተፍ የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች:-
1. ተጫራቹ በሚወዳደሩባቸው ለእያንዳንዱ ቦታ(ኮድ) በታሸገ ኤንቨሎፕ ቴክኒካል ሰነድ እና ፋይናሻል ሰነድ ኦርጅናልና ኮፒ) ማቅረብ አለባቸው፡፡
2. የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO) ከሚያቀርቡት ዋጋ ላይ 10% ማስያዝ አለባቸው፡፡
3. በጨረታው ላይ መወዳደር የሚፈልጉ ድርጅቶች /ግለሰቦች/ ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ሰዓት ከሰኞ እስከ አርብ (ከ2፡00-11፡00) እና ቅዳሜ እስከ 6፡00 ሰዓት /ስድስት ሰዓት/ የማይመለስ ብር 300.00 (ሶስት መቶ ብር) ብቻ በጥሬ ገንዘብ በመክፈል የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ መውሰድ የሚችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
4. ጨረታው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 (አስራ አምስት) ተከታታይ የስራ ቀናት አየር ላይ የሚውል ሆኖ በዕለቱ (በአስራ አምስተኛው ቀን) 4፡00 ተዘግቶ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎች በተገኙበት ይከፈታል፡፡ የመክፈቻው ቀን ዕሁድ/በዓል ላይ የሚውል ከሆነ ቀጣይ የስራ ቀን የሚከፈት ይሆናል።
5. ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ፡- 22 እየሩስ ህንጻ ከሚገኘው የድርጅቱ ዋና መ/ቤት 8ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 8-01
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር፡- 011-666-33-67 መደወል ይችሳሱ፡፡
ለተጨማሪ መረጃ የደርጅቱን ማህበራዊ ድረ-ገፃች ይጎብኙ፦
Facebook: https://www.facebook.com/citybus 2015
Telegram: https://t.me/citbus
አዲስ አበባ የከተማ አውቶቡስ አገልግሎት ድርጅት
