አልወሳኢል ትሬዲንግ ኃ/የተ/የግ/ማህበር ከመስከረም 2009 ዓ.ም እስከ ጥር 2018 ዓ.ም ድረስ ያለውን የድርጅቱን ሂሳብ በውጭ ኦዲተር ማሰራት ይፈልጋል።
የኦዲት ጨረታ ማስታወቂያ
አልወሳኢል ትሬዲንግ ኃ/የተ/የግ/ማህበር ከ መስከረም 2009 ዓ.ም እስከ ጥር 2018 ዓ.ም ድረስ ያለውን የድርጅቱን ሂሳብ በውጭ ኦዲተር ማሰራት ይፈልጋል። በመሆኑም ከዚህ በታች የተመለከቱት መስፈርቶችና መረጃዎች የምታሟሉ ሕጋዊ ኦዲተሮች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 7 ተከታታይ የስራ ቀናት ከጠዋቱ 3፡00 እስከ ምሽቱ 11፡00 ሰዓት ከዚህ በታች በተጠቀሰው ቢሮአችን በታሸገ ኤንቨሎፕ የመወዳደሪያ ሰነድ ማቅረብ ይቻላል።
የመወዳደሪያ መስፈርቶች
· የታደሰ የኦዲት የንግድ ሙያ ፈቃድ
· የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ያለው
· ከዚህ በፊት ኦዲት ያደረጉትን ድርጅት የስራ ልምድ ማቅረብ የሚችል።
በዚህም መሰረት ለምትሰጡት አገልግሎት የምትጠይቁትን የገንዘብ መጠን (ታክስን ጨምሮ) እንዲሁም የአመቱን የሂሳብ ምርመራ ጨርሳችሁ ምታስረክቡበትን ቀን በመጥቀስ በታሸገ ፖስታ በድርጅቱ ቢሮ ማቅረብ ትችላላችሁ፡፡
አድራሻ፡- ቂርቆስ ክ/ከተማ ወረዳ 05፣ ቡልጋሪያ የትራፊክ መብራት አካባቢ
ለበለጠ መረጃ፡- 09-11-99-34-47
አልወሳኢል ትሬዲንግ ኃ/የተ/የግ/ ማህበር
