Tender Detail

Tender Details


በደ/ም/ኢ/ህ/ክ/መ/በዳውሮ ዞን የታርጫ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በ2018 በጀት ዓመት ከዚህ በታች በዘርፉ የተዘረዘሩትን የሥልጠና ዕቃዎችን በአገራዊ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።


የጨረታ ማስታወቂያ

የግዥ/የጨረታ መለያ ቁጥር ታፖቴኮ/05/2018 .

 

በደ//////በዳውሮ ዞን የታርጫ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ 2018 በጀት ዓመት ከዚህ በታች በዘርፉ የተዘረዘሩትን የሥልጠና ዕቃዎችን በአገራዊ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

·        ሎት 1. የአይሲቲ፣ ኤሌክትሮኒክሲ እና የኤሌክትሪክ ዕቃዎች

·        ሎት 2. የጨርቃ ጨርቅ ቆዳና የቆዳ ውጤቶች እና ማሽነሪዎች

·        ሎት 3. የግንባታ የውሃና ፈሳሽ መስመር፣ ብረታ ብረትና ማሽነሪዎች

·        ሉት 4. የአውቶሞቲቭ ዕቃዎችና ማሽነሪዎች

·        ሎት 5. የእንስሳት እርባታ ዕቃዎች

ስለዚህ በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች፣

1.     በመስኩ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድና የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ኮፒ ማቅረብ የሚችሉ፣

2.     የተጨማሪ እሴት ታክስና የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችሉ፣

3.     የዘመኑን ግብር ስለመክፈሉ እና በጨረታ ይሳተፉ ደብዳቤን ከሚመለከተው አካል ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣

4.     የዕቃ ግዥ አቅራቢነት የምስክር ወረቀት እና በድረ-ገጽ የተመዘገቡበትን ማስረጃ ሰነድ ኮፒ ማቅረብ የሚችሉ፣

5.     የጨረታ ሰነድ 200.00 /ሁለት መቶ ብር ብቻ/ በኮሌጃችን የንግድ ባንክ አካውንት ቁጥር 1000042580647 ላይ ገቢ በማድረግ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከታወጀበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ በሥራ ሰዓት ቀርበው በታርጫ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ //አስ//ሥሂ 1 ፎቅ ቢሮ ቁጥር 02-16 ላይ መውሰድ ይችላሉ፣

6.     የጨረታ ማስከበሪያ ለእያንዳንዱ ሎት 3,000.00 /ሦስት ሺህ ብር ብቻ/ ሲሆን ከታወቀ ባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO) በታርጫ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ስም በማዘጋጀት ከቴክኒካል መረጃ ፖስታ ጋር አንድ ላይ በማሸግ ማቅረብ አለበት፤

7.     ተጫራቾች በፖስታ የቴክኒካል መረጃ ኮፒ ለየብቻ፣ የፋይናንሻል መረጃ አሪጅናልና አንድ ኮፒ የብቻ ሞልቶው በማሸግ ሁሉንም መረጃ በአንድ እናት ፖስት አሽጎ በኮሌጁ 1 ፎቅ ቢሮ ቁጥር 02-16 ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ መክተት ይኖርባቸዋል፣

8.     የጨረታ ሣጥኑ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከታወጀበት ቀን ጀምሮ 15 ተከታታይ ቀናት ከተቆጠረ 16ኛው ቀን ከጠዋቱ 400 ሰዓት ታሽጎ በዕለቱ 430 ሰዓት ተጫራቾች በተገኙበት የሚከፈት ስሆን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባይገኙም የጨረታ መክፈት ሂደቱን አያስተጓጉልም፣

9.     የጨረታ ዋጋ ፀንቶ የሚቆየው አሸናፊው ተጫራች ተለይቶ ከታወቀበትና ውል ከተገባበት ቀን ጀምሮ 60 ቀናት መሆኑን ማወቅ ይኖርባቸዋል፣

10. ተጫራቾች የሚጫረቱበት ዋጋ በገዙበት ሠነድ ባለው ዋጋ ማቅረቢያ ቦታ ላይ የአንዱን ዕቃ ከሻት በፊት ከሞሉ ቫትን ጨምሮ ጠቅላላ ዋጋ ግልጽ በሆነ በሚነበብ ጽሁፍ ሞልቶ ማቅረብ ይኖርበታል፣

11. ተጫራቾች በሚያቀርቡት የመወዳደሪያ ዋጋ ዝርዝር ሠነድ ላይ ስርዝ ድልዝ ሳይኖር ስምና አድራሻቸውን የፋክስና ስልክ ቁጥራቸውን ጽፈው በድርጅታቸው ማህተምና በፊርማቸው ማረጋገጥ ይኖርባቸዋል፣

12. የጨረታው አሸናፊ ተጫራች አሸናፊነቱ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ 7 የስራ ቀናት ውስጥ ያሸነፈበትን የዕቃውን ጠቅላላ ዋጋ 10% የውል ማስከበሪያ ዋስትና በማስያዝ ከኮሌጁ ጋር ውል መግባት ይኖርባቸዋል፣

13. በጨረታው የተሸነፉ ተወዳዳሪዎች ያስያዙት ሲፒኦ (CPO) ወዲያውኑ የሚመለስ ሲሆን የአሸናፊዎች ግን ከኮሌጁ ጋር የውል ስምምነት ሲፈፀሙና የውል ማስከበሪያ ጠቅላላ ዋጋ 10% ሲያስይዙ የሚመለስ ይሆናል፣

14. አሸናፊ ተጫራቾች ያሸነፉበትን ዕቃ እስከ ኮሌጅ ድረስ በራሳቸው ወጪ አጓጉዘው ማቅረብ አለበት፣

15. የጨረታ ማስታወቂያ የተጫራቾች መመሪያ ሆኖ ያገለግላል፣

16. ኮሌጁ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብት አለው።

 

በደ//////በዳውሮ ዞን የታርጫ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ

Save Tender