Tender Detail

Tender Details


በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ የመርካቶ ቁጥር 1 የህግ ማስከበር ቅ/ጽ/ቤት በ2018 በጀት ዓመት የሚያስፈልገውን ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ዕቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።


ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

 

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ የመርካቶ ቁጥር 1 የህግ ማስከበር //ቤት 2018 በጀት ዓመት የሚያስፈልገውን፣

·        ሎት አንድ፡- የፅሕፈት መሣሪያዎች

·        ሎት ሁለት፡- የጽዳት እቃዎች

·        ሎት ሶስት፡- አልባሳት

·        ሎት አራት፡- የኤሌክትሮኒክስና የአይቲ ዕቃዎች

·        ሎት አምስት፡- የመኪና እቃዎች

·        ሎት ስድስት፡- የህንጻ መሳሪያዎች

·        ሎት ሰባት - የመስተንግዶ አቅርቦቶች

·        ሎት ስምንት፡- ህትመቶች

·        ሎት ዘጠኝ፡ የኮምፒውተር፤ የፕሪተር፤ የኮፒ ማሽንና ዩፒኤስ ሰርቭስና ጥገና የእጅ ዋጋ

·        ሎት አስር፡- የኮምፒውተር የፕሪተር፤ የኮፒ ማሽንና የዕቃው ዋጋ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

ስለሆነም በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልግና የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟላ ማንኛውም ህጋዊ ተጫራች በጨረታው መወዳደር ይችላል።

1.     ህጋዊ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ።

2.     የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመንግስት ግዥና ንብረት ማስወገድ አገልግሎት ባዘጋጀው የዕቃና አገልግሎት አቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተካተቱና ለዚህም ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።

3.     ግብር የመክፈል ግዴታቸውን የተወጡ መሆኑን የሚያረጋግጥ በግብር አስገቢው ባለሥልጣን የተሰጠ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።

4.     ለተጨማሪ እሴት ታክስ የተመዘገቡ መሆኑን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት።

5.     ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 10 የስራ ቀናት ቅዳሜን ጨምሮ የጨረታውን ሰነድ የማይመለስ ብር 100 /አንድ መቶ ብር/ በመክፈል በሥራ ሰዓት ...አ.. ቢሮ መርካቶ ቁጥር 1 የህግ ማስከበር //ቤት በግዥና ፋይናንስ የሥራ ሂደት ቢሮ ልደታ ዊዝደም የገበያ ማዕከል ህንፃ 4 ፎቅ ቢሮ ቁጥር 403 በመቅረብ መውሰድ ይችላሉ።

6.     ተጫራቾች በወሰዱት ሰነድ መሠረት የሚወዳደሩበትን ዋጋ በሰም በታሸገ ኢንቨሎፕ በማድረግ ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ቅዳሜን ጨምሮ በተጠቀሰው ቢሮ ለጨረታ በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።

7.     ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ የጠቅላላውን ዋጋ 2% በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ መርካቶ .1 /////ቤት |Addis Ababa City Government Revenue Office Merkato No.1 M.TPB.Office/ በሚል ስም በማዘጋጀት በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም ሁኔታዎች ላይ ያልተመሠረተ የባንክ ጋራንቲ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

8.     ጨረታው ጥር 22 ቀን 2018 .. ከጠዋቱ 400 ሰዓት ተዘግቶ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጥር 22 ቀን 2018 .. ከጠዋቱ 430 ሰዓት ይከፈታል።

9.     ቅርንጫፍ /ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

 

ተጨማሪ መረጃ፡- 011-5579160 በመደወል መረጃ ማግኘት ይቻላል፡፡ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ የመርካቶ ቁጥር 1 //ቤት

አድራሻ፡- ደታ ዊዝደም የገበያ ማዕከል ህንፃ 4 ፎቅ ዥና ፋይናንስ የሥራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 403 መጠየቅ ይችላሉ።

 

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ የመርካቶ ቁጥር 1 የህግ ማስከበር //ቤት

Save Tender