በኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት በምዕራብ አርሲ ዞን የቆሬ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በ 2018 በጀት ዓመት ለማዘጋጃ አስፓልት ዳር የመንገድ መብራት በ"Electromechanical Contractor Grade Five and above" ለመግዛት ይፈልጋል።
የጨረታ ማስታወቂያ
በኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት በምዕራብ አርሲ ዞን የቆሬ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በ 2018 በጀት ዓመት ለማዘጋጃ አስፓልት ዳር የመንገድ መብራት በ"Electromechanical Contractor Grade Five and above" ስለሚፈልግ።
1. ተወዳዳሪዎች በዕቃ አቅራቢነት ዝርዝር መመዝገባቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ከሚመለከተው አካል ማቅረብ የሚችሉና እንዲሁም የተ/እ/ታ ተጠቃሚ መሆናቸውን ማስረጃ ፎቶ ኮፒ ማቅረብ አለባቸው።
2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን ነምበር) ያላቸው መሆን አለባቸው፡፡
3. ተወዳዳሪዎች ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 /አስራ አምስት/ ተከታታይ የሥራ ቀናት ሊወዳደሩበት የጨረታ ሰነድ በማይመለስ ብር 1,500.00 (አንድ ሺ አምስት መቶ) ብር ከ ቆሬ ከተማ አስ/ ገቢዎች ጽ/ቤት መግዛት ይችላሉ፡፡
4. ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ በ 4፡30 ሰዓት ፖስታው ታሽጎ በተዘጋጀ ሳጥን ገቢ ሆኖ በዚሁ ዕለት በ 5:00 ሰዓት ተወዳዳሪዎች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ባይገኙም ጨረታውን ከመክፈት አያግድም። ዕለቱ በዓል ወይም ቅዳሜና እሁድ ላይ ከዋለ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይሆናል።
5. ተወዳዳሪዎች የጨረታውን ሰነድ አንድ ኦርጂናል እና ሁለት ፎቶ ኮፒ በማድረግ በአንድ እናት ኤንቨሎፕ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
6. ተጫራቾች /ተወዳዳሪዎች/ ተወዳድረው አሸናፊ በሆኑበት እስከ ቤቱ ድረስ በራሳቸው ማጓጓዣ ማድረስ ይጠበቅባቸዋል፡፡
7. ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉት ከላይ የተጠቀሱትን ዝርዝር ነገሮችን አሟልተው ሲገኙ ብቻ ይሆናል።
8. ተጫራቾች ማሸነፋቸውን ጨረታውን በደብዳቤ ከተገለጸላቸው በ5 ቀን ውስጥ ከመ/ቤቱ ጋር ውል መፈራረም ግዴታ አለባቸው።
9. ተጫራቾች በሚያቀርቡት ሰነድ ላይ አድራሻ፣ ስም፣ ፊርማ ማህተምና ልዩ ቁጥር ስልክ ቁጥር ማስፈር ይጠበቅባቸዋል።
10. ተወዳዳሪዎች የሚያቀርቡት ማንኛውንም ዕቃ ጥራታቸው በኢትዮጵያ ደረጃዎች ኤጀንሲ የተረጋገጠ መሆን አለባቸው፡፡
11. ተጫራቾች ያስገቡትን መረጃና ሰነድ የእኔ አይደለም ማለት አይችሉም፡፡
12. ተጫራቾች ሰነድ የገዙበትን ደረሰኝ ከነዳቸው ጋር ማያያዝ አለባቸው፡፡
13. ተወዳዳሪዎች በገዙት ሰነድ ላይ ያለ ምንም ስርዝ ድልዝ በተዘጋጀ ቦታ ላይ መሙላትና ማህተም ማድረግ አለባቸው።
14. መ/ቤቱ ናሙና እንዲቀርብባቸው ከሰነድ ጋር ተያይዞ የቀረቡትን ዕቃዎች የማምጣት ግዴታ አለባቸው።
15. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
16. ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥሮች፣ 0916107688 እና 0913447850 ደውሎ ማረጋገጥ ይቻላል።
በኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት በምዕራብ አርሲ ዞን የቆሬ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት
