የሰሜን ሸዋ ዞን ገንዘብ መምሪያ ለ2018/2019 የምርት ዘመን አገልግሎት የሚውል የአፈር ማዳበሪያ በዞኑ ሥር ለሚገኙ የህ/ስ/ማህበራት ጣቢያ መጋዘን ድረስ ለማጓጓዝ እንዲቻል ብቃት ያላቸውን የጭነት አገልግሎት ሰጪ ትራንስፖርት ድርጅቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ የአገልግሎት ግዥውን ለመፈጸም ይፈልጋል።
የብሔራዊ ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
የሰሜን ሸዋ ዞን ገንዘብ መምሪያ ለ2018/2019 የምርት ዘመን አገልግሎት የሚውል የአፈር ማዳበሪያ በዞኑ ሥር ለሚገኙ የህ/ስ/ማህበራት ጣቢያ መጋዘን ድረስ ለማጓጓዝ እንዲቻል ብቃት ያላቸውን የጭነት አገልግሎት ሰጪ ትራንስፖርት ድርጅቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ የአገልግሎት ግዥውን ለመፈጸም ይፈልጋል።
በመሆኑም በዞኑ ሥር ለሚገኙ የተለያዩ ዩኒየኖች ከየማዕከላዊ መጋዘኖቻቸው በሥራቸው ለሚገኙ የህ/ስ/ማህበራት መጋዘን ድረስ ለማጓጓዝ ሲሆን በሥራው ላይ ለመሣተፍ የሚፈልጉ የደረቅ ጭነት ማመላላሻ ባለንብረቶች ማህበር በአዲሱ አደረጃጀት መሠረት የብቃት ማረጋገጫ ከሚመለከተው አካል በማቅረብ መጫረት የሚችሉ ሲሆን ተጫራቾች የማጓጓዣ ታሪፋቸውን በማራገፊያ ጣቢያዎች ዝርዝር መሠረት በታሸገ ፖስታ የመጫረቻ ሰነዳቸውን በማቅረብ መሣተፍ የሚችሉ ሲሆን የጨረታ ግምገማው በተናጠል የሚካሄድ ይሆናል። ስለሆነም ተጫራቾች በጨረታው ለመሣተፍ ማሟላት ያለባቸው ግዴታዎች -
1. በዘርፉ የተሠማሩበት ህጋዊ የታደሠ የንግድ ሥራ ፈቃድ ያላቸው፤
2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር / TIN / ያላቸው፤
3. የግዥው መጠን ከብር 200,000.00 /ሁለት መቶ ሺህ ብር / በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ /VAT/ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምሰክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል ፤
4. በጨረታው የሚሣተፉ ተጫራቾች ከ70 ኩንታል በላይ የሚጭኑ ተሸከርካሪዎች የሚያቀርቡ ከሆነ ከፌደራል ትራንስፖርት ባለሥልጣን ተመዝግበው የተደራጁ ሆነው በዘመኑ የታደሠ የብቃት ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችሉ እንዲሁም ተጫራቾች የሚያቀርቡት ከ70 ኩንታል በታች ከሆነ በክልል ትራንስፖርት ቢሮ ተመዝግበው የተደራጁ ሆነው በዘመኑ የታደሠ የብቃት ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችሉ፤
5. የተሽከርካሪ ዝርዝር፤ የሠሌዳ ቁጥር ፤ የመኪናው ዓይነትና የመጫን አቅም የሚያስረዳ ከፌደራል ትራንስፖርት ባለሥልጣ ወይም ከክልል ትራንስፖርት ቢሮ የተሰጠ የ2018 ዓ/ም ወቅታዊ የታደሠ ምዝገባ ፈቃድ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፤
6. ተጫራቾች በጨረታው ለመሣተፍ ከላይ ከተራ ቁጥር 1 እስከ 5 ድረስ የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
7. የሚጓጓዘው የአፈር ማዳበሪያ ዓይነት፤ መጠን፤ የኪሎ ሜትር ርቀትና ሌሎች ዝርዝር መረጃዎች ከጨረታ ሰነዱ ላይ ማግኘት ይቻላል።
8. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ከሰሜን ሸዋ ዞን ገንዘብ መምሪያ ቢሮ ቁጥር 22 ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ዕለት አንስቶ በሚቆጠር እስከ 16ኛው ቀን ድረስ ዘወትር በሥራ ሠዓት ለእያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 300.00 /ሦስት መቶ ብር/ ብቻ በመክፈል መግዛት ይቻላል።
9. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ ለሚወዳደሩበት የአገልግሎት ግዥ የሞሉትን የጠቅላላ ዋጋ 1% በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ ሲፒኦ / C.P.O / ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ በሰሜን ሸዋ ዞን ገንዘብ መምሪያ ሥም ማስያዝ አለባቸው።
10. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ ለ60 ቀናት ተይዞ የሚቆይ ሆኖ መሠራት ይኖርበታል።
11. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን በጥንቃቄ በማሸግ በሰሜን ሸዋ ዞን ገንዘብ መምሪያ የግዥና ንብ/አስ/ቢሮ ቁጥር 22 ድረስ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ዘወትር በሥራ ሠዓት ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ዕለት አንስቶ እስከ 16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ድረስ ማስገባት ይችላሉ።
12. የጨረታ ሣጥኑ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡01 ታሽጎ በዚሁ ዕለት ከጠዋቱ 4፡30 በሰሜን ሸዋ ዞን ገንዘብ መምሪያ የመሰብሰቢያ አዳራሽ የሚከፈት ሲሆን የመክፈቻው ቀን የሥራ ቀን ላይ ካልዋለ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሣሣይ ሠዓት የሚከፈት ይሆናል ።
13. መሥሪያ ቤቱ የሚያወዳድረው ለአንድ መሠረታዊ ማህበር ለአንድ ኩንታል በሚያቀርበው የነጠላ ዋጋ ሲሆን አንድ ተጫራች በተዘረዘሩት ሁሉም ወረዳዎች በሚገኙ የመሠረታዊ ህ/ስ/ማህበራት የመጫረቻ ዋጋ ሞልቶ መመለስ ያለበት ሲሆን ከፋፍሎ ዋጋ በመሙላት መጫረት አይቻልም።
14. መሥሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታው በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ መሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
15. በጨረታው ለመሣተፍ የሚፈልጉ ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 22 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 011-681-32-41 ወይም 011-681-63-96 በመደወል ማማኘት ይቻላል።
የሰሜን ሸዋ ዞን ገንዘብ መምሪያ
ደ/ብርሃን
