የኢትዮጵያ የክፍያ መንገዶች ኢንተርፕራይዝ የደረሰኞች ህትመት አገልግሎት ግዥ በጨረታ አወዳድሮ ለመፈጸም ይፈልጋል።
የጨረታ ማስታወቂያ
የሀገር ውስጥ ግልፅ ጨረታ ቁጥር 29/2018
1. የደረሰኞች ህትመት አገልግሎት ግዥ
በመሆኑም በጨረታው መሳተፍ የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች የሚከተሉትን ሕጋዊ ሰነዶች ማሟላት ይኖርባቸዋል፡-
· የታደሰ ንግድ ፍቃድ
· ቫት ተመዝጋቢ
· ታክስ ክሊራንስ
· በግዥ ባለሥልጣን የምዝገባ ማስረጃ
· የታክስ ከፋይነት ምዝገባ ሠርተፍኬት
· በዘርፉ የአቅራቢነት ምዝገባ ሠርተፍኬት ወረቀት
· ጨረታው ፀንቶ የሚቆየው ለ 30 (ሰላሳ) ቀናት
· የጨረታ ማስከበሪያ መጠን 30,000.00 (ሰላሳ ሺ) ብር ሆኖ የጨረታ ማስከበሪያው በሲ.ፒ.አ ወይንም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና መሆን ይኖርበታል።
· ሰነድ ለመግዛት የምትፈልጉ ተጫራቾች ሰነዱ በሚገኝበት በኢትዮጵያ የክፍያ መንገዶች ኢንተርፕራይዝ ዋና መስሪያ ቤት በግዥ ክፍል ቢሮ, ቁጥር 01 የማይመለስ 300.00 (ሶስት መቶ) ብር በመክፈል መውሰድ ትችላላችሁ፡፡
· የጨረታ ማስረከቢያ የመጨረሻ ቀን እና ሰዓት 03/06/2018 ዓ.ም እስከ ቀኑ 9፡00 ሰዓት
· ጨረታው የሚከፈተው፡- በዕለቱ 03 /06/2018 ዓ.ም ከቀኑ 9፡30 ሰዓት
· ኢንተርፕራይዙ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
· ለበለጠ መረጃ እና ማብራሪያ ዋናው መስሪያ ቤት በአካል በመገኘት ወይም በስልክ 0114171703 መጠየቅ ይቻላል፡፡
አድራሻ፡-
· ዋና መስሪያ ቤት
ቱሉ ዲምቱ
የኢትዮጵያ የክፍያ መንገዶች ኢንተርፕራይዝ
