የኮልፌ ቅዱስ ራጉኤል አዲስ ሕይወት አክሲዮን ማህበር ባሰራቸው ሕንፃዎች ላይ ለአስተዳደር የሚሆኑ ቢሮዎችን በዘመናዊ መልኩ ለማሰራትና የሕንፃውን የተለያዩ ክፍት ቦታዎች ለሱቅ አገልግሎት እንዲመቹ አጥንቶ የሚያቀርብ ባለሙያ በጨረታ አወዳድሮ አሸናፊውን ለማስጠናት ይፈልጋል።
በድጋሚ የወጣ የአስተዳደር ቢሮ እና ለሱቅ የሚሆኑ ክፍት ቦታዎች ጥናት ጨረታ ማስታወቂያ
የኮልፌ ቅዱስ ራጉኤል አዲስ ሕይወት አክሲዮን ማህበር ባሰራቸው ሕንፃዎች ላይ ለአስተዳደር የሚሆኑ ቢሮዎችን በዘመናዊ መልኩ ለማሰራትና የሕንፃውን የተለያዩ ክፍት ቦታዎች ለሱቅ አገልግሎት እንዲመቹ አጥንቶ የሚያቀርብ ባለሙያ በጨረታ አወዳድሮ አሸናፊውን ለማስጠናት ይፈልጋል።
በዚሁ መሠረት በመስኩ ልምድ ያላችሁ የህንፃ ምህንድስና ዲዛይን (Arcthectural design) ሙያተኞች በአካል በመገኘት ሕንፃውን አይታችሁ መጥታችሁ መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
ተጫራቾች ማማላት የሚገባቸው መስፈርቶች:
1. በዘርፉ 2018 ዓ.ም የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ እና የንግድ ምዝገባ ሰርተፊኬት፣
2. የቫት እና የግብር ከፋይነት ሰርቲፈኬት (TIN Number)፣
3. ለሚከፈለው ክፍያ ህጋዊ ደረሰኝ ማቅረብ የሚችል፤
4. በተመሳሳይ ሥራ የስራ ልምድ ማቅረብ የሚችል፣
ከላይ የተጠቀሱትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተወዳዳሪዎች የጨረታው ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ 10 (በአስር) የስራ ቀናት የምታጠኑበትን የሥራ ዋጋና አስፈላጊ ሰነዶች በታሸገ ኤንቨሎፕ አክሲዮን ማህበሩ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 4 ማስገባት ትችላላችሁ።
5. ጨረታው ከወጣበት ቀን አስረኛው ቀን 8፡00 ሰአት ተዘግቶ በዛው ቀን 9፡00 ሰአት ላይ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በአክሲዮን ማህበሩ ጽ/ቤት ይከፈታል፡፡ የመክፈቻ ቀን አ/ማህበሩ ለተወዳዳሪዎች በስልክ ያሳውቃል፡፡
6. የጨረታው አሸናፊ በማስታወቂያ ከተገለፀ በ2 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ አክሲዮን ማህበሩ ጽ/ቤት በአካል በመቅረብ ውል መዋዋል ይጠበቅበታል፡፡ ይህ ካልሆነ ግን ስራውን በራሱ ፈቃድ እንደተወ ይቆጠራል።
ማሳሰቢያ፡-
· ማህበሩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፈልም ሆነ ሙሉ ለሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
· አድራሻ፡-በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 10 ልዩ ቦታው አጠና ተራ ከቴሌው ጀርባ ባለው የአ/ማህበሩ የገቢያ ማዕከል ሕንፃ ቁጥር 2 አራተኛ ፎቅ የቢሮ ቁጥር 4
· ለተጨማሪ መረጃ ስልክ ቁጥር 09-12-05-47-92/09-32-08-03-77
የኮልፌ ቅዱስ ራጉኤል አዲስ ሕይወት አክሲዮን ማህበር
