የኮልፌ ቅዱስ ራጉኤል አዲስ ሕይወት አክሲዮን ማህበር ለ3 ዓመት የአክሲዮን ማህበሩን ሂሳብ በውጭ ኦዲተር አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡
የኦዲተር የጨረታ ማስታወቂያ
የኮልፌ ቅዱስ ራጉኤል አዲስ ሕይወት አክሲዮን ማህበር ለ3 ዓመት የአክሲዮን ማህበሩን ሂሳብ በውጭ ኦዲተር አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡
ስለዚህ ማንኛውም ከዚህ በታች የተገለፁት መስፈርቶችን የምታሟሉ ተጫራቾች በጨረታው መጫረት የምትችሉ መሆኑን እንገለፃለን፡፡
1. የንግድ መለያ ቁጥር፣
2. የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት፣
3. የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣
4. የብቃት ማረጋገጫ እና የሥራ ልምድ ማሳየት ወይም መረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣
5. የAABE መረጃ የሚያቀርብ (የኢትዮጵያ ሂሳብ አያያዝና አዲት ቦርድ የምዝገባ ምስክር ወረቀት) ማቅረብ የሚችሉ፡፡
6. ተጫራቾች የሚያቀርቡት የሚወዳደሩበትን ወይም የሚያቀርቡትን ዋጋ በሰም በታሸገ ኤንቬሎፕ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 (አስራ አምስት) ተከታታይ የሥራ ቀናት ከታች በተገለፀው ሰዓት ሙሉ መረጃቸውን ኦሪጅናሉንና ኮፒ በመያዝ በኮልፌ ቅዱስ ራጉኤል አዲስ ሕይወት አክሲዮን ማህበር ፅ/ቤት ቢሮ ቁጥር 4 ማስገባት ትችላላችሁ፡፡
7. ቦርዱ ካወዳደረ በኋላ ያለፈውን በማስታወቂያና በስልክ የምናሳውቅ ይሆናል፡፡
ማስታወሻ፡-
· ጠዋት 2፡30 ሰዓት እስከ 6፡30 ሰዓት -ከሰዓት ከ7፡30- ሰዓት እስከ 10፡30 ሰዓት
አድራሻ፡- ኮልፌ አጠና ተራ ከቴሌኮሙኒኬሽን ጀርባ የኮልፌ ቅዱስ ራጉኤል አዲስ ሕይወት አክሲዮን ማህበር ብሎክ 2 4ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 4
ስልክ 09-63-37-10-45 ወይም 09-12-05-47-92
የኮልፌ ቅዱስ ራጉኤል አዲስ ሕይወት አክሲዮን ማህበር
