የመንግስት ልማት ድርጅቶች አስተዳደር ባለስልጣን ለኮንስትራክሽን ዲዛይንና ማማከር ድርጅት ቢዝነስ ሞዴል ጥናት፣ ለህዝብ መዝናኛ ቦታዎችና ፓርኮች ኮርፖሬሽን፣ ለኢግዚቢሽንና ማዕከል ድርጅት እና ለቄራዎች ድርጅት አቻ የሀብት ግመታ እና የሲኒማ ቤቶች አስተዳደር ድርጅት አይ ኤፍ አር ኤስ/ IFRS/ ጥናትና ትግበራ በግልፅ ጨረታ ማሰራት ይፈልጋል።
ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር የመ/ል/ድ/አስ/ባለ/ግ/ ጨረታ 003/2018
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመንግስት ልማት ድርጅቶች አስተዳደር ባለስልጣን
የአገልግሎት ግዥ የጨረታ ማስታወቂያ
የመንግስት ልማት ድርጅቶች አስተዳደር ባለስልጣን ለኮንስትራክሽን ዲዛይንና ማማከር ድርጅት ቢዝነስ ሞዴል ጥናት፣ ለህዝብ መዝናኛ ቦታዎችና ፓርኮች ኮርፖሬሽን፣ ለኢግዚቢሽንና ማዕከል ድርጅት እና ለቄራዎች ድርጅት አቻ የሀብት ግመታ እና የሲኒማ ቤቶች አስተዳደር ድርጅት አይ ኤፍ አር ኤስ/ IFRS/ ጥናትና ትግበራ በግልፅ ጨረታ ማሰራት ይፈልጋል።
ስለሆነም፣
ሎት -1- የኮንስትራክሽንና፣ ዲዛይንና ማማከር ድርጅት ቢዝነስ ሞዴል ጥናት
ሎት 2- የህዝብ መዝናኛ ቦታዎችና ፓርኮች ኮርፖሬሽን አቻ የሀብት ግመታ በድጋሚ የወጣ
ሎት 3-ኢግዚቢሽን ማዕከል ድርጅት አቻ የሀብት ግመታ
ሎት 4- የቄራዎች ድርጅት አቻ የሀብት ግመታ
ሎት 5- የሲኒማ ቤቶች አስተዳደር ድርጅት አይ ኤፍ አር ኤስ /IFRS/ ጥናትና ትግበራ
⁕ ተጫራቾች በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው እና የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆን አለባቸው።
⁕ ተጫራቾች በፋይናንስ ቢሮ ዌብሳይት በአቅራቢዎች ዝርዝር ላይ የተመዘገቡ መሆን አለባቸው።
⁕ ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ያስገቡትን የጠቅላላ ዋጋውን 1% በተወዳደሩበት ሎት በየሎቱ በCPO ማስያዝ አለባቸው።
⁕ ተጫራቾች የቫት ተመዝጋቢ ሆነው ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችሉና መለያ ቁጥር /ቲን ነምበር/ ያላቸው መሆን አለባቸው።
⁕ የጨረታ አሸናፊ አሸናፊነቱን ሲገለፅለት ያሸነፈበትን ከጠቅላላ ዋጋ 10% የውል ማስከበሪያ በCPO ማስያዝ አለባቸው።
⁕ ተጫራቾች ጋዜጣው ከወጣባት ቀን ጀምሮ ብር 500 /አምስት መቶ ብር/ በመክፈል ፒያሳ ከሚገኘው ዋስትና የንግድ ማዕከል ህንፃ 8ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 8/03 የግዥና ንብረት አስተዳደር ጠቅላላ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት ቢሮ በመቅረብ ለ15 ተከታታይ የስራ ቀናት ድረስ የጨረታ ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ።
⁕ ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሰነዳቸውን ቴክኒካል እና ፋይናሽያል ለየብቻው ዋናውን እና ኮፒ በታሸገ ኤንቨሎፕ በማደረግ የጨረታ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 16ኛው የስራ ቀን 4፡00 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
⁕ ጨረታው የሚዘጋበት ቀን የጨረታ ማስታወቂያ በወጣ በ16ኛው የስራ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ታሽጐ በዛኑ ቀን ጠዋት 4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ወይም በሌሉበት በባለስልጣኑ የመሰብሰቢያ አዳራሽ 4ኛ ፎቅ ይከፈታል።
⁕ መስሪያ ቤቱ ጨረታውን በከፊልም ይሁን መሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
⁕ ዘግይቶ የመጣ የጨረታ ፖስታ ተቀባይነት የለውም።
አድራሻ:- ፒያሳ የሚገኘው ዋስትና የንግድ ማዕከል ህንፃ 8ኛ ፎቅ የመንግስት ልማት ድርጅቶች አስተዳደር ባስስልጣን
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር፡- 0111124485
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመንግስት ልማት ድርጅቶች አስተዳደር ባለስልጣን
