በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት የጉራጌ ዞን ፋይናንስ መምሪያ ለጉራጌ ዞን ትምህርት መምሪያ የተማሪ መማሪያ መጽሀፍ ህትመት ከቅድመ 1ኛ-8ኛ ክፍል መማሪያ መጽሀፍ በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 6/2018
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት የጉራጌ ዞን ፋይናንስ መምሪያ ለጉራጌ ዞን ትምህርት መምሪያ የተማሪ መማሪያ መጽሀፍ ህትመት
1 ከቅድመ 1ኛ-8ኛ ክፍል መማሪያ መጽሀፍ በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታው መወዳደር ይችላሉ።
1. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፣
2. የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣
3. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN Number) ያላቸው፣
4. የአቅራቢነት የምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ
5. የግዢው መጠን ከብር 500,000 /አምስት መቶ ሺ ብር/ በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣
6. ተጫራቾች በጨረታው ለመሣተፍ ከላይ ከተራ ቁጥር 1 5 የተጠቀሰውንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፣
7. ለሚወዳደሩባቸው ዕቃዎች ናሙና ሲጠየቅ ማቅረብ አለባቸው፣
8. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ብር 500,000 /አምስት መቶ ሺህ/ በባንክ በተመሰከረለት CPO ከቴክኒካል ኦርጅናል ዶክመንት ጋር አያይዘው በጉራጌ ዞን ፋይናንስ መምሪያ ስም ተዘጋጅቶ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
9. ተጫራቾች ከላይ የተጠቀሰውን የጨረታ ሰነድ ለመግዛት የምትፈልጉ የማይመለስ ብር 300 /ሶስት መቶ ብር/ በጉራጌ ዞን ገቢዎች መምሪያ በመክፈል ሰነዱን ከጉራጌ ዞን ፋ/መምሪያ ግዥ ንብ/አስ/የስራ ሂደት ሁለተኛ ፎቅ በመቅረብ መግዛት ይችላሉ፣
10. ማንኛውም ተጫራች ዕቃውን ጉራጌ ዞን ፋ/መምሪያ ወልቂጤ ከተማ ድረስ ለማቅረብ የሚያስችል ዋጋ የሚያሳይ የጨረታ ሰነድ ለቴክኒካል አንድ ኦሪጅናልና ሁለት ኮፒ እና ለፋይናንሻል አንድ ኦሪጅናልና ሁለት ኮፒ በማለት በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በጥንቃቄ ታሽጐ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት ጉራጌ ዞን ፋ/መምሪያ ግዥ ንብ/አስ/የሥራ ሂደት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ዘወትር በሥራ ሰዓት እስከ ቀኑ 11፡30 ሰዓት ድረስ ማስገባት አለባቸው።
11. ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት በ16ኛው ቀን እስከ 6፡00 ሰአት ድረስ የጨረታ ሰነድ ማስገባት ይችላሉ። ጨረታ የሚከፈትበት ቀን በዚሁ ቀን ከቀኑ 6፡00 ሰዓት የጨረታ ሳጥኑ ታሽጐ በዚሁ ዕለት ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በጉራጌ ዞን ፋይናንስ መምሪያ አዳራሽ በይፋ ይከፈታል። ጨረታው የሚከፈትበት ቀን በአል ወይም ቅዳሜና እሁድ ቀን ላይ ከዋለ ወደሚቀጥለው የስራ ቀን የሚሸጋገር መሆኑን እንገልጻለን።
12. መ/ቤቱ በጨረታው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
13. ለበለጠ መረጃ መ/ቤቱ ድረስ በአካል በመቅረብ ወይም በስልክ ቁጥር 011-3300112 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።
ማሳሰቢያ፡- የጨረታ ማስከበሪያ ቢድ ቦንድ ለምታቀርቡ ተጫራቾች 90 ቀንና ከዚያ በላይ መሆን ይጠበቅበታል።
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት የጉራጌ ዞን ፋይናንስ መምሪያ
