የዘመን ክንስትራክሽን ኮርፖሬሽን የደንብ ልብስ እና የፅዳት ዕቃዎች ለመግዛት ይፈልጋል።
ደንብ ልብስ እና ፅዳት ዕቃዎች ግዥ ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ ግልፅ ጨረታ ቁጥር 10/18
የዘመን ክንስትራክሽን ኮርፖሬሽን የደንብ ልብስ እና የፅዳት ዕቃዎች ለመግዛት ይፈልጋል።
ስለዚህ በጨረታው ለመሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች፡-
1. በዘርፍ የታደሰ የንግድ ፈቃድ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር እና የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ የምስክር ወረቀት ያላቸው
2. የጨረታ ሰነዱን ባ/ዳር ከተማ ዘመን ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን ቀበሌ 11 ኮብል አክሲዮን ማህበር ፊት ለፊት ወደ ዲያስፖራ በሚወስደው መንገድ በሚገኘው የኮርፖሬሽኑ ህንጻ እና አ/አበባ አመልድ ህንፃ 7ኛ ፎቅ በሚገኘው ማስተባበሪያ ጽ/ቤት በመገኘት ብር 200.00 /ሁለት መቶ ብር ከፍሎ በመውሰድ ከጨረታ ሰነዱ ዝርዝር ሁኔታውን በማንበብ የጨረታ መመሪያው በሚያዘው መሰረት ጨረታውን መሙላት አለባቸው።
3. የጨረታ ሰነድ ማስገቢያና መክፈቻ ባ/ዳር ከተማ ዘመን ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን ቀበሌ 11 ኮብል አክሲዮን ማህበር ፊት ለፊት ወደ ዲያስፖራ በሚወስደው መንገድ በሚገኘው የድርጅቱ ህንጻ ሲሆን የጨረታ መዝጊያና መክፈቻ ቀን ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15 ተከታታይ ቀናት ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ድረስ ብቻ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል። የጨረታ መዝጊያ ቀን በ15ኛው ቀን 8:00 ይዘጋና በዚያኑ ቀን 8፡30 ይከፈታል። 15ኛው ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን እስከ ቀኑ 8፡00 ሰዓት ድረስ ማስገባት የሚኖርባቸው ሲሆን የጨረታ ሳጥኑ በዚያኑ ቀን 8:00 ሰዓት ተዘግቶ 8:30 ይከፈታል።
4. የጨረታ ማስከበሪያ ከቫት ጋር የጠቅላላ ዋጋውን 2% በባንክ በተረጋገጠ (CPO) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
5. ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።
ስልክ ቁጥር 058 321 7806 / 09 27-60 55 99 / 09 18-49 05 45
ባ/ዳር የዘመን ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን
የአዲስ አበባ ማስተባበሪያ ቅ/ጽ/ቤት /09 18 70 5 03/
የዘመን ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን
