Tender Detail

Tender Details


በልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 08 ፋይናንስ ጽ/ቤት በ2018 በጀት ዓመት የሁለተኛ ዙር ግልጽ ጨረታ አላቂ የቢሮ እቃዎች፣ የደንብ ልብስ፤ የጽዳት እቃዎች፣ የቋሚ አላቂ እቃዎች፣ ቋሚ እቃዎች፣ ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፣ የአገልግሎት ግዥዎችን አቅራቢዎችን አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡


የሁለተኛ ዙር ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር 002/2018

 

በልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 08 ፋይናንስ ጽ/ቤት በ2018 በጀት ዓመት የሁለተኛ ዙር ግልጽ ጨረታ አላቂ የቢሮ እቃዎች፣ የደንብ ልብስ፤ የጽዳት እቃዎች፣ የቋሚ አላቂ እቃዎች፣ ቋሚ እቃዎች፣  ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፣ የአገልግሎት ግዥዎችን አቅራቢዎችን አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

በዚህ መሰረት፡-

1.     ተጫራቾች የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆኑን አግባብ ያለው የታደሰ ንግድ ፈቃድ እናከግዥ ኤጀንሲ በእቃ አቅራቢነት በኦንላይን የተመዘገቡበትን ምስክር ወረቀት እና የቫትተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ መረጃ ከጨረታ ሰነድ ጋር አያይዘው ማስገባትይኖርባቸዋል፡፡

2.     ተጫራቾች ከጨረታ መዝጊያ ቀን እና ሰዓት ቀደም ብለው ናሙና የሚያስፈልጋቸውእቃዎችን እንዲሁም የፎቶ ናሙና የሚያፈልጋቸው እቃዎች በፎቶ ማቅረብ ይኖርባቸዋል። ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ የጨረታው ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የሚታሰብ 10/አስር/ የስራ ቀናት ውስጥ የማይመለስ 500/አምስት መቶ ብር/ በመክፈል ሰነዱን መግዛት ይኖርባቸዋል።

3.     ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ብቻ ማስያዝ የሚቻል ሲሆን ለሎት /1/ አላቂ የቢሮ እቃዎች 15000/አስራ አምስት ሺህ ብር/፣ ለሎት /2/ ደንብ ልብስ 10000/አስር ሺህ ብር/፣ ለሎት /3/ የጽዳት እቃዎች 15000/አስራ አምስት ሺህ ብር/፣ ለሎት 4/ቋሚ እቃዎች 15000/አስራ አምስት ሺህ ብር/፣ ለሎት 5 የቋሚ አላቂ እቃዎች 5000 አምስት ሺህ ብር/፣ ለሎት 6 የአገልግሎት ግዥ 5000 /አምስት ሺህ ብር/ ሲሆን የሁሉም ሎት በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡ ከሲፒኦ ውጭ ሌላ የጨረታ ማስከበሪያ አንቀበልም፡፡

4.     ተጫራቾች የሚወዳደሩበት የጨረታ አይነት ውስጥ የተዘረዘሩት እቃዎችን ዋጋ ሲሞሉ ከቫት ጋር እያንዳንዱ እቃ ዋጋ ድምር በጨረታ ሰነዱ ላይ በአለው የዋጋ መጠየቂያ ረድፍ በግልጽ ስርዝ ድልዝ ሳይኖር ማስቀመጥ ይኖርባቸዋል፡፡

5.     ተጫራቾች በተዘጋጀው የጨረታ ሰነድ ብቻ በመጠቀም የመወዳደሪያ ዋጋቸውን ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ በሌላ ቅጽ የሚጠቀሙ ተጫራቾች ጨረታ ውስጥ እንዳይሳተፉ ይደረጋሉ።

6.     ተጫራቾች መሉ ስማቸውን አድራሻቸውን የድርጅቱን ሙሉ ስም በእያንዳንዱ ሰነድ ላይ በመፈረም ማቅረብ ይኖርባቸዋል፤ ሰነዶችን በማህተም ማረጋገጥ አለባቸው፡፡

7.     የጨረታውን አካሄድ ለማዛባት የሚሞክሩ ተጫራቾች ከጨረታ ውጭ ይደረጋሉ፡፡ ለወደፊቱም የመንግስት ግዥ ጨረታ ላይ እንዳይሳተፍ ይደረጋሉ፡፡ የአስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ወዲያውኑ ለመንግስት ገቢ ይደረጋል፡፡

8.     ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ተጫራቾች በአቀረቡት የጨረታ መወዳደሪያ ሀሳብ ወይም ማሻሻያ ማድረግ እንዲሁም ከጨረታው ራሳቸውን ማግለል አይችሉም፡፡

9.     ተጫራቾች ከላይ የተጠየቁትን ማስረጃዎች አሟልተው አሽገው አንድ ኦርጅናልና አንድ ኮፒ ልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 05 ፋይናንስ ጽ/ቤት 6ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 25 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡

10.  ተጫራቾች የአቅራቢነት ሰርተፍኬት ኮፒ ከጨረታ ሰነዱ ጋር አያይዘው ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡

11.  ጨረታው በአስረኛው የስራ ቀን 10፡30 ሰዓት ተዘግቶ በአስራ አንደኛው ቀን በስራ ቀን 4፡30 ላይ ህጋዊ ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው በተገኙበት የጨረታ ሳጥኑ ይከፈታል፡፡

12.  ጨረታውን የአሸነፈ አካል ማሸነፉ እንደተገለፀበት ከ7 የቅሬታ ቀናት በኋላ ከመስሪያ ቤቱ ጋር ውል መፈፀም ይኖርበታል፡፡

13.  ተጫራች በጨረታ ሰነዱ ላይ በተጠቀሱት እቃዎች ዝርዝር በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ መጫረት ይችላሉ፡፡

14.  ጨረታው ከተዘጋ በኋላ የሚቀርቡ የጨረታ ሰነዶች ተቀባይነት አይኖራቸውም፡፡

15.  መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ከአገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

16.  ተጫራቾች በሚወዳደሩበት የእቃ አይነት ለአንድ እቃ አንድ ሳምፕል ብቻ ማቅረብ ይኖርበታል።

እቃ አይነት ሁለት ሳምፕል የአቀረበ ተጫራች ከውድድር ውጭ ይደረጋል፡፡

አድራሻ፡- ብስራተ ገብርኤል ቤተክርስቲያን ወረድ ብሎ ብሩክ ክሊኒክ 200 ሜትር ገባ ብሎ

ልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 08 አስተዳደር 6ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 25 ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር 0118329662

 

ልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 08 አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት

Save Tender