ጣና በለስ ስኳር ፋብሪካ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ነገሮች በብሔራዊ ግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
የጨረታ ማስታወቂያ
ብሔራዊ ግልፅ ጨረታ ቁጥር: ጣበስፋ/አግ/ብግጨ/06/2018
ጣና በለስ ስኳር ፋብሪካ
በሎት-1 ዳም ትራክ ብዛት 16፣ ሲንግል ካፕ ብዛት 02፣ ደብል ካፕ ብዛት 01፣ መለስተኛ አውቶቡስ ብዛት 02 እና 7,000 ሊትር የሚይዝ ቦቲ ብዛት 02 ለ45 ቀናት ለመከራየት እና
በሎት-2 የተለያዩ ጐማና የውስጥ ላስቲኮች
በሎት-3 የልብስ ሣሙና 200 gm ብዛት 90,000 በብሔራዊ ግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
1. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ብቁ ተጫራቾች ህጋዊ የ2018 ዓ.ም የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የዘመኑን ግብር መክፈላቸውን የሚያረጋግጥ ከግብር ሰብሳቢው ባለሥልጣን የተሰጠ የታክስ ክሊራንስና በጨረታ መሳተፍ የሚያስችል የድጋፍ ደብዳቤ/ የምስክር ወረቀት፣ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር፤ ለተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆኑን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት በተጨማሪም ተጫራቾች የመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ ወይም ሌላ አግባብነት ያለው አካል ባዘጋጀው የዕቃና አገልግሎት አቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ መካተታቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው።
2. ጨረታው የካቲት 30 ቀን 2018 ዓ.ም ከረፋዱ 4፡00 ሰዓት ላይ ይዘጋል። ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዶቻቸውን በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ጨረታው ከመዘጋቱ በፊት ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል። ጨረታው በጨረታው መክፈቻ ላይ መገኘት የሚፈልጉ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከታች በተራ ቁጥር 4 በተገለፀው አድራሻ የካቲት 30 ቀን 2018 ዓ.ም ከረፋዱ 4:30 ሰዓት ላይ ይከፈታል። ዘግይቶ የሚቀርብ የመጫረቻ ሰነድ ውድቅ ይደረጋል።
3. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ የማይመለስ ብር 400.00 (አራት መቶ ብር) በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሂሳብ ቁጥር 1000057735167 በመከፈልና የባንክ አድቫይስ በማቅረብ በተራ ቁ. 4 ከተመለከተው ቢሮ መግዛት ይችላሉ።
4. የጨረታው ማስረከቢያና መክፈቻ አድራሻ ቀጥሎ የተመለከተው ነው።
አዲስ አበባ ቶታል 3 ቁጥር ማዞሪያ ተዘንአ ሆስፒታል አካባቢ
የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ህንጻ።
ብሎክ A ቢሮ ቁጥር B008
ስልክ ቁጥር 011 5-58-67-25
አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ
5. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ በየሎቱ የጠቅላላ ዋጋውን 2% ብር በባንክ የተረጋገጠ የክፍያ ሰነድ ሲፒኦ (CPO) ወይም በሁኔታዎች ላይ ባልተመሠረተ የባንከ ዋስትና (ጋራንቲ) ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
6. ጨረታው ፀንቶ የሚቆየው ጨረታው ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ ለ60 ቀናት ነው።
7. የጨረታው ማስከበሪያ ዋስትና ፀንቶ የሚቆይበት ጊዜ ጨረታው ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ ለ90 ቀናት ነው።
ፋብሪካው ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፈል የመሠረዝ መበቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ በስልከ ቁጥር 011558-67-25 ደውሎ መጠየቅ ይችላል።
ጣና በለስ ስኳር ፋብሪካ
