የሀዋሳ ማዕከላዊ ማረሚያ ተቋም ለህግ ታራሚዎች አገልግሎት የሚውል ማገዶ እንጨት በዘርፉ ከተሠማሩ ነጋዴዎች አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
የጨረታ ማስታወቂያ
የሀዋሳ ማዕከላዊ ማረሚያ ተቋም ለህግ ታራሚዎች አገልግሎት የሚውል ማገዶ እንጨት በዘርፉ ከተሠማሩ ነጋዴዎች አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
በዚሁ መሠረት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ነጋዴዎች መወዳደር ይችላሉ።
1. በዚህ ዘርፍ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸው የዘመኑ ግብር የከፈሉ፣ ተጨማሪ እሴት ታከስ ተመዝጋቢ፣ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ያላቸውና ለአቅራቢነት የተመዘገቡ የንግድ ምዝገባ ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
2. በጨረታው የሚሳተፉ ተጫራቾች ከላይ የተጠቀሱትን ማገዶ እንጨት ለ6 ወራት የሚፈለገው መጠን ጥራትንና ደረጃውን በጠበቀ መልኩ በየወሩ እስከ ተቋሙ ቅጥር ግቢ ድረስ አምጥተው ማስረከብ ይኖርባቸዋል፡፡
3. ማንኛውም ተጫራች በተራ ቁጥር 1 የተገለፁትን ህጋዊ ማስረጃዎች ለጨረታው ከሚቀርበው ዋጋ ጋር ዋናውንና ኮፒውን አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
4. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ በሁኔታዎች ላይ ያልተመሠረተ በባንክ በተረጋገጠ CPO 50,000 (ሃምሳ ሺህ) ብር ከዋናው ሰነድ ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
5. የጨረታው ሰነድ ዋናውንና ኮፒውን በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በሰነድ ላይ በተገለፀው አድራሻ በተከታታይ 15 ቀናት ለዚሁ በተዘጋጀ ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
6. የጨረታው ሳጥን የሚታሸገው በአስራ አምስተኛ ቀን 4፡00 ሰዓት ሲሆን የጨረታ ሳጥን የሚከፈተው በዕለቱ ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበትም ሆነ ባልተገኙበት ይከፈታል። ይህ ቀን የበዓልም፣ ቅዳሜ ወይም እሁድ ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ከላይ በተገለፀው ተመሳሳይ ሰዓት ታሽጎ ይከፈታል፡፡
7. ማንኛውም ተጫራች የእህል ናሙና ጨረታው ከመከፈቱ አንድ ቀን ቀደም አድርጎ በማስገባት ጥራቱን ለጨረታ ኮሚቴ ማሳየት አለበት፡፡
8. ተጫራቾች ከሀዋሳ ማዕከላዊ ማረሚያ ተቋም ግ/ፋ/ንብ/አስ/ደ/ሥ/ሂደት ቀርበው ዝርዝር ሰነዱን 100 (አንድ መቶ) ብር በማይመለስ ብር በመክፈል መግዛት ይኖርባቸዋል፡፡
ማሳሰቢያ፡- መ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ተጨማሪ መረጃ-በስልክ ቁጥር- 046-122-80-84 እና 0913287411 መደወል ይችላሉ፡፡
በሲዳማ ብሔራዊ ክልል መንግስት የሀዋሳ ማዕከላዊ ማረሚያ ተቋም
