በሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ጤና መምሪያ አዳሬ አጠቃላይ ሆስፒታል B+G+8 ሕንፃን ሊፍት አሳንሰር ሥራ በጨረታ አወዳድሮ ለማሠራት ይፈልጋል፡፡
3ኛ ዙር የወጣ የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
በሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ጤና መምሪያ አዳሬ አጠቃላይ ሆስፒታል B+G+8 ሕንፃን ሊፍት አሳንሰር ሥራ በጨረታ አወዳድሮ ለማሠራት ይፈልጋል፡፡
ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ተፈላጊ መመዘኛዎችን የሚያሟሉ ሕጋዊ ተጫራቾች በጨረታው እንዲሳተፉ ይጋብዛል፡፡
1. በኤሌክትሮ መካኒካል (Electro-mechanical) ሥራ ተቋራጭ ደረጃ 1
2. ተጫራቾች በሥራ መስክ ሕጋዊ የታደሰ የንግድ ፍቃድ የንግድ ምዝገባ ወረቀት ሰርተፍኬት (certificate of registration) ማቅረብ የሚችሉና የዘመኑ ግብር መከፈላቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
3. ተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ የሆኑ
4. አቅራቢነት የምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው፡፡
5. የታክስ ክፍያ ክሊራንስ ማስረጃ (tax clearance) ማቅረብ አለባቸው።
6. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ 500,000 (አምስት መቶ ሺህ) ብር በባንክ የተረጋገጠ ጋራንት ወይም የተመሰከረ ሲፒኦ (CPO) ወይም ቢድ ቦንድ (bid bond) ለእያንዳንዱ ሎት ጨረታ ከሰነድ ጋር ማቅረብ አለበት፡፡
7. የጨረታ ሰነዱ ከአዳሬ አጠቃላይ ሆስፒታል ግዢ እና ክፍያ ፋይናንስ ክፍል በማቅረብ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 (ለአስራ አምስት) ለተከታታይ ቀናት የማይመለስ ብር 1000 (አንድ ሺህ) ብር በመክፈል መግዛት ይቻላል፡፡
8. የጨረታ ሰነድ በሰም ለየብቻቸው በታሸገ ኤንቨሎፕ ቴክኒካል እና ኦርጅናል እና ሁለት ኮፒ እና ፋይናንሻል አንድ ኦርጅናል እና ሁለት ኮፒ በድምሩ ስድስት ፖስታ ወይም ኤንቨሎፕ ሁሉም ላይ ፊርማና የድርጅቱ ማኅተም የተደረገበት በመያዝ አዳሬ አጠቃላይ ሆስፒታል ግዢና ክፍያ ፋይናንስ ወይም ግዢ ኬዝ ቲም ከፍል ለዚህ ጨረታ በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
9. ጨረታው በዚህ ቀን በእለቱ ከቀኑ 8፡00 ሠዓት ታሽጎ ጨረታው በዚሁ ቀን 8፡30 ሠዓት ተጫራች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ሆነ ባልተገኙበት አዳሬ አጠቃላይ ሆስፒታል ግዢ እና ክፍያ ፋይናንስ ክፍል ይከፈታል ይህ ቀን ቅዳሜና እሁድ ከሆነ ሰኞ እንዲሁም በበዓላት ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይከፈታል።
10. በጨረታ አከፋፈት ሥነ-ሥርዓት የተነበበው ዋጋ እና አርቲሚቲክ ቼክ በሚደረግበት ጊዜ በሁለቱ መካከል ከ2% በላይ ሆነ በታች ልዩነት ካለ በቀጥታ ከጨረታ ውጪ ይደረጋል፡፡
11. ከጨረታ በላይ ባለው ጠቅላላ ዋጋ 10 % (አስር ፐርሰንት) በላይ የዋጋ ቅናሽ (Rebate) የተደረገ ከሆነ በቀጥታ ከጨረታ ውጭ ይደረጋል፡፡
12. ተጫራቹ ከመሐንዲስ ግምት 15% (አስራ አምስት ፐርሰንት) በታችና በላይ ያቀረበ ከሆነ ከጨረታ ውጪ ይሆናል፡፡
13. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ ለመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ መረጃ ስልክ 0462208202/0462204566
የአዳሬ አጠቃላይ ሆስፒታል /ሀዋሳ/
