ኢካፍኮ አ.ማ. የ2018፤ 2019 እና 2020 በጀት ዓመት ሂሣቦችን የሚመረምሩለት ኦዲተሮች ይፈልጋል
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 003/2018
በድጋሚ የወጣ የሂሣብ ምርመራ ጨረታ ማስታወቂያ
ኢካፍኮ አ.ማ የ2018 ፤ 2019 እና 2020 በጀት ዓመት ሂሣቦችን የሚመረምሩለት ኦዲተሮች መምረጥ ስለፈለገ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች በማሟላት መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።
1. የታደሰ የዘርፉ ንግድ ፈቃድ፤
2. የሙያ ብቃት ማረጋገጫ፤
3. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር
4. በኢካፍኮ አ/ማ የስራ ዘርፍ (በፈርኒቸር ማንፋክቸሪንግ፤ በጋረዥ አገልግሎትና በግንባታ ስራ) የኦዲቲንግ በቂ የሥራ ልምድና ባለሙያ ስለመኖሩ ማረጋገጫ፤
5. የእያንዳንዱ በጀት ዓመት ሒሳብ መርምሮ ሪፖርት ለማቅረብ የሚፈጀው የስራ ቀናት በመግለፅ መወዳደር አለባቸው።
ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ 2% የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በሲፒኦ ማስያዝ አለባቸው። ጨረታው በሁለት ኤንቨሎፕ የሚካሄድ በመሆኑ ተጫራቾች ለሒሳብ ምርመራው አገልግሎቱ የሚያስከፍሉትን ዋጋ ከሌሎች ሰነዶች ለብቻ ለይቶ በማሸግ ከመጋቢት 11 ቀን 2018 ዓ.ም.8፡00 ሰዓት በፊት ለዚሁ በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይጠበቅባቸዋል። ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት መጋቢት 11 ቀን 2018 ዓ.ም. በ8፡30 ሰዓት ይከፈታል።
አክሲዮን ማህበሩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረ ውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አዲስ አበባ ስልክ ቁጥር፡-011 442 1775
ኢካፍኮ አክሲዮን ማህበር
