Tender Detail

Tender Details


የኢትዮጵያ ልማት ባንክ በአዋጅ ቁጥር 97/90፣ 216/92 እና 1147/2011 መሠረት በብድር ዕዳ ምክንያት የተረከበውን ከዚህ በታች በሰንጠረዡ የተዘረዘረውን ንብረት በድርድር ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።


የጨረታ ማስታወቂያ

ቁጥር 003/2018

 

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ በአዋጅ ቁጥር 97/90 216/92 እና 1147/2011 መሠረት በብድር ዕዳ ምክንያት የተረከበውን ከዚህ በታች በሰንጠረዡ የተዘረዘረውን ንብረት በድርድር ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።

 

.

የተበዳሪው የመያዣ ሰጪው ስም

የንብረት/ፕሮጀክት አድራሻ

የንብረት/ ፕሮጀ ዝርዝር

የቦታ ስፋት (በሄክታር)

የጨረታ መነሻ ዋጋ (በብር)

የጨረታ ሁኔታ

የጨረታ ደረጃ

ጨረታው የሚካሄድበት ቀንና ሰዓት

1

ኤም ዋይ ሹዝ ኤንድ ሌዘር ማኑፋክቸሪንግ /የተ/የግል/

አማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ደብረ ብርሃን ከተማ 09 ቀበሌ

የጫማ እና የቆዳ ማምረቻ ፋብሪካ (በትግበራ ላይ ያለ) የሕንፃ ግንባታዎች፣ ማሸነሪዎች እና የኤሌክትሪክ ሥራዎች

6.83 ሄክታር

ብር 397,968,817.12 (ሦስት መቶ ዘጠና ሰባት ሚሊዩን ዘጠኝ መቶ ስልሳ ስምንት ሺህ ስምንት መቶ አስራ ሰባት ብር ከአስራ ሁለት ሳንቲም)

ድርድር

ሁለተኛ

መጋቢት 21 ቀን 2018 . ከጠዋቱ 400-600 ሰዓት

2

ማጃንግ ግሮ ኢንዱስትሪ /የተ/የግል ማህበር

ጋምቤላ ///መ፡ ማጃንግ ዞን፣ መንገሺ ወረዳ፣ አሽኔና ባያ ቀበሌ

የመስኖ እርሻ እና ግንባታዎች፣ የእርሻ ማሽነሪዎች፣ ተሽከርካሪዎች፣ 145 ሄክታር ላይ የተተከለ የሙዝ ቋሚ ተክል ያለው

1000 ሄክታር በሊዝ የተገኘ መሬት

375,513,976.00 (ሶስት መቶ ሰባ አምስት ሚሊዮን አምስት መቶ አስራ ሶስት ሺህ ዘጠኝ መቶ ሰባ ስድስት ብር)

ድርድር

ሁለተኛ

መጋቢት 22 ቀን 2018 . ከጠዋቱ 400-600 ሰዓት

 

ማሳሰቢያ፡-

1.     ተጫራቾች የማይመለስ ብር 100 /አንድ መቶ ብር/ በመፈል የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ በመግዛት ንብረቶቹን የሚገዙበትን ዋጋ፣ ስምና አድራሻቸውን በፎርማቱ ላይ በመጥቀስ በባንኩ ዋና /ቤት ሁለተኛ ታወር ምድር ቤት ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀው ሣጥን ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣ ከሦስተኛው ቀን ጀምሮ ለኤም ዋይ ሹዝ ኤንድ ሌዜር ፋብሪካ እስከ መጋቢት 21 ቀን 2018 . ከጠዋቱ 350 ሰዓት፣ እና ለማጃንግ አግሮ ኢንዱሰትሪ እስከ መጋቢት 22 ቀን 2018 . ሆኖ ለሁሉም ከጠዋቱ 350 ሰዓት ድረስ በማስገባት፤ ከቀኑ 400-600 ባለው ጊዜ ውስጥ ቀርበው መደራደር ይችላሉ፡፡

2.     ተጫራቾች የጨረታውን መነሻ ዋጋ 10 በመቶ በባንክ ፍያ ማዘዣ /../ ብቻ በማስያዝ መጫረት ይችላሉ፡፡

3.     አሸናፊ የሆነው ተጫራች ያሸነፈበትን ቀሪ ገንዘብ 15 /በአስራ አምስት/ ተከታታይ ቀናት ውስጥ ጠቃሎ ፈል ይኖርበታል፤ በዚህ ጊዜ ውስጥ ካልከፈለ ያስያዘው ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ሆኖ ጨረታው ይሰረዛል፡፡

4.     ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በሰንጠረዡ በተመለከተው ቀንና ሰዓት በባንኩ ዋናው /ቤት ታወር ሁለት 5 ፎቅ በሚገኘው መሰብሰቢያ አዳራሽ ይካሄዳል፡፡ ሕጋዊ ሰውነት ያላቸው አካላትን ወክሎ በጨረታው ለመሳተፍ የሚቀርብ ሰው የማህበሩ መመስረቻ ጽሑፍ/መተዳደሪያ ደንብ ከእነ ማሻሻያዎቹ (ካለ) የንግድ ምዝገባ፣ የንግድ ፍቃድ፣ ሌሎች አስፈላጊ ማስረጃዎችን እና የተረጋገጠ የውክልና ሥልጣን ሰነዶችን ይዞ መቅረብ ይኖርበታል፡፡

5.     15% የተጨማሪ እሴት ታክስና ሌሎች ገዢ እንዲከፍላቸው በሕግ የተወሰኑ ፍያዎችን፣ የስም ማዛወሪያ ፍያን ጨምሮ ገዢው ይከፍላል፡፡

6.     ንዳንድ የድርጅቱ ንብረቶች የጉምሩክ ቀረጥና ታክስ ያልተከፈለባቸው ስለሆኑ ገዢው የቀረጥ ነጻ ሊኖረው አሊያም የሚፈለገውን ቀረጥ/ታክስ ለመንግሥት ለመክፈል ይገደዳል፡፡

7.     የማጃንግ አግሮ ኢንዱስትሪ /የተ/የግ/ማህበር የሥራ እንቅስቃሴ ያልተቋረጠ በመሆኑ እሸናፊው ከግዢው ዋጋ በተጨማሪ ያልተሰበሰበ ወይም ምችት ላይ ያለ የሙዝ ምርት በርክክ ወቅት በሚደረስበት የትመና ዋጋ መሠረት በጥሬ ገንዘብ መግዛት ይችላል፡፡

8.     ተጫራቾች ንብረቱን ለመጎብኘት ከፈለጉ አስቀድሞ ከባንኩ ጋር ቀጠሮ በመያዝ ከጨረታው ቀን በፊት መነብኘት ይችላሉ፡፡

9.     ባንኩ ለሽያጭ የቀረቡትን ንብረቶች የሚሸጠው ከተቻለ ሙሉ በሙሉ በጥሬ ገንዘብ ሲሆን አሸናፊው በባንከ ብድር ፖሊስ መሠረት አስፈላጊውን መስፈርቶች ካሟላና ፕሮጀክቱን የሚያስቀጥል ከሆነ ንብረቱን በከፊል ብድር ለመግዛት መጠየቅ ይችላል፡፡

10. የጨረታ ሸናፊው የማጃንግ አግሮ ኢንዱስትሪ /የተ/የግ/ማህበርን ቋሚ ሠራተኞች በሙሉ ከመብትና ጥቅማቸው ጋር መረከብ ይጠበቅበታል፡፡

11. የንብረቱ ስመ-ንብረት ለገዥው እንዲዞር ባንኩ ለሚመለከተው መንግሥታዊ አካል ደብዳቤ ይፅፋልገዥው ጉዳዩን ተከታትሎ ያስፈፅማል

12. በጨረታው ላይ መገኘት የሚችሉት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው ብቻ ናቸው

13. በጨረታው ዝርዝር እና ተጨማሪ መረጃን ለማግኘት የኢትዮጵያ ልማት ባን ዋና /ቤት ታወር ሁለት ሦስተኛ ፎቅ ላይ በሚገኘው የኦንጎይንግ ኮንሰርን ፕሮጀክትስ እና አኳየርድ አሴትስ ማኔጅመንት ዳይሬቶሬት በአካል በመቅረብ ወይም በስልከ ቁጥር 011-524-53-73/ 011-524-42-69 ደውሎ ማግኘት ይቻላል፡፡ የመያዣ ንብረቶቹን ብኘት የሚፈልግ ከዳይሬክቶሬቱ ጋር አስቀድሞ ቀጠሮ በመያዝ ብኘት ይቻላል

14. ባንኩ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው

 

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ

Save Tender