በኮ/ቀ/ክ/ከተማ የወረዳ 02 የህዳሴ አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት በ2018 ዓ.ም በጀት ዓመት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን እቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 002/2018
በኮ/ቀ/ክ/ከተማ የወረዳ 02 የህዳሴ አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት በ2018 ዓ.ም በጀት ዓመት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን እቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
ሎት 1. የደንብ ልብስ፣ ሎት 2. አላቂ የቢሮ የጽህፈት እቃዎች፣ ሎት 5. አላቂና ቋሚ የት/ት እቃዎች፣ ሎት 6. የጽዳት እቃዎች፣ ሎት 15. ለልዩ ልዩ ክፍያዎች በዚህ መሰረት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርት የምታሟሉ ተጫራቾች መሳተፍ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡
1. ተጫራቾች ከስራው ዘርፍ ጋር አግባብነት ያለው የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያለው የዘመኑ ግብር መክፈላቸውን የሚገልጽ ወቅታዊ ሰርተፍኬት የአቅራቢነት ሰርተፍኬት ማቅረብ እና የዘመኑ ደረሰኝ /QR/ ያለው እና ማቅረብ የሚችል።
2. ት/ቤቱ በሚሸጠው ሰነድ ላይ ያለውን ማንኛውንም መመሪያ በማጤን እና የሚመለከተውን በመሙላት፣ ማህተም በማድረግ ሰነዱን በሙሉ በታሸገ ፖስታ ዋናውንና ፎቶ ኮፒውን በተለያየ ፖስታ በማድረግ በኮ/ቀ/ክ/ከተማ ወረዳ 02 የህዳሴ አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ቢሮ ቁጥር 7 በተዘጋጀዉ የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይጠበቅበታል፡፡
3. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ለመግዛት በየሎቱ የማይመለስ 100 ብር /አንድ መቶ ብር/ ከፍለው መውሰድ ይችላሉ፡፡
4. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ የጨረታ ማስከበሪያ /cpo/ የብር መጠን በየሎት ለእያንዳንዱ ሎት1. 2,000፣ ሎት2. 5,000፣ ሎት5. 8,000፣ ሎት6. 5,000፣ ሎት15. 2,000 ማስያዝ አለባቸው።
5. በጥቃቅን አነስተኛ ተቋማት የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ በጨረታ ማስከበሪያ በውል ማስከበሪያ እና በቅድሚያ ከፍያ ዋስትና ምትክ ካደራጀው ተቋም በኃላፊ ብቻ የተፈረመ የዋስትና ደብዳቤ ተቀባይነት ሲኖረው በስራ ሂደት የሚፈረም ደብዳቤ ተቀባይነት የለውም፡፡
6. ማንኛውም ተጫራች በሚጫረቱበት እቃ ላይ የሚያቀርቡት የእቃ ናሙና በግልፅ የሚታይ ፎቶ ቦታው ላይ እና ሰነዱ ላይ በወጣው መሰረት ማሳየት እና ማቅረብ አለበት።
7. ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ ቀናት ቅዳሜና እሁድን ጨምሮ በአየር ላይ ቆይቶ በ11ኛው ቀን በ3፡30 ታሽጎ በ4፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባሉበት በፋይናንስ ክፍል/ቢሮ ይከፈታል፡፡
መስ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል /በሙሉ/ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ፡- ካራቆሬ ወደ መድሃኒዓለም ቤተክርስቲያን መሄጃ ፖሊስ ጣቢያውን አለፍ ብሎ
ተጨማሪ መረጃ:- 0113695428/
በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ የወረዳ 02 የህዳሴ አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ፋይናንስ/ግዥ/ቢሮ
