የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ትምህርት ቢሮ በሞዳሊቲ-2 ከደረጃ 1 እና ደረጃ 2 ላሉ ተማሪዎች የመማሪያና ማስተማሪያ መጻህፍት ህትመት በመስኩ የተሰማሩ ድርጅቶችን አወዳድሮ ለማሳተም ይፈልጋል፡፡
የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ትም/ቢሮ ጨረታ ቁጥር 04
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ትም/ቢሮ በ2018 በጀት ዓመት በዩኒሴፍ በጀት
በመጠቀም
በሞዳሊቲ-2 ከደረጃ 1 እና ደረጃ 2 ላሉ ተማሪዎች የመማሪያና ማስተማሪያ መጻህፍት ህትመት በመስኩ የተሰማሩ ድርጅቶችን አወዳድሮ ለማሳተም ይፈልጋል፡፡
በዚሁ መሰረት ጨረታው ላይ ለመሳተፍ የሚችሉ ተጫራቾች
1. በዘርፉ ህጋዊ የንግድ ፍቃዳቸውንና የምዝገባ ሰርተፊኬታቸውን ያሳደሱ በግብር ከፋይነት ተመዝግቦ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያለውና ተጨማሪ እሴት ታክስ የተመዘገቡበትን የምዝገባ ወረቀት፣ የዘመኑን የግብር ግዴታውን የተወጣ እና በአቅራቢዎች ዝርዝር የተመዘገበበት እና የታክስ ክሊራንስ ደብዳቤ ማቅረብ የሚችል፣ መረጃ ፎቶ ኮፒ አያይዞ ማቅረብ ይጠበቅበታል፡፡
2. ተጫራቾች ትምህርት ቢሮ ቁጥር 18 በመቅረብ ለሥራው የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ እያንዳንዱን ብር 500.00 /አምስት መቶ ብር/ በመክፈል ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት ዘወትር በሥራ ሰዓት መግዛት ይችላሉ፡፡
3. የፋይናንሻል እና ቴከኒካል ሠነዶቻቸውን ኦርጅናል እና አንድ ኮፒ ሰነድ ለየብቻ አሽጎ በማቅረብ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በቢሮ ቁጥር 18 ለዚህ በተዘጋጀ ሣጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
4. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና CPO ወይም የባንክ ጋራንቲ የሚገልጽ የገንዘብ መጠን ብር 80,000.00 /ሰማኒያ ሺህ ብር/ ጨረታ ማስከበሪያ ማቅረብ አለባቸው፡፡
5. ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት ቆይቶ በ16ኛው የሥራ ቀን ከቀኑ 6፡30 ሰዓት ታሽጎ 8፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል። 16ኛው ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ የስራ ቀን የሚከፈት ይሆናል፡፡
6. መ/ቤቱ በጨረታው ላይ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር፡- 0487752359/0916863055 መጠየቅ ይችላሉ፡፡
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት
ትም/ቢሮ
