የአዋሽ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት የጉምሩከ ህግን ተላልፈው የተያዙ የተለያዩ የኮንትሮባንድ እቃዎችን በ09/07/2018 ዓ/ም በግልጽና በሐራጅ ጨረታ በኦከሸን ኢትዮጵያ(auction ethiopia) መተግበሪያ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።
የጨረታ ማስታወቂያ
የአዋሽ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት የጉምሩከ ህግን ተላልፈው የተያዙ የተለያዩ የኮንትሮባንድ እቃዎችን በ09/07/2018 ዓ/ም በግልጽና በሐራጅ ጨረታ በኦከሸን ኢትዮጵያ (auction ethiopia) መተግበሪያ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።
በመሆኑም በጨረታው መሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች መተግበሪያውን ከአፕ ስቶር ወይም ፕሌይ ስቶር auction Ethiopia ብለው በማውረድ ወይም www.auction.et ላይ በመመዝገብና የጨረታ ሰነዱን በማየት፣ የሚከተሉትን ዝርዝር መስፈርቶች በማሟላት በጨረታው መሳተፍ የምትችሉ ሲሆን፣ የእቃዎችን ሳምፕልም ከኦክሽን ኢትዮጵያ ድረ-ገጽ (auction ethiopia page) ወይም አዋሽ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት በአካል በመገኘት ወይም በቴሌግራም እንዲላክሎት በማድረግ ማየት የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን።
የጨረታ መስፈርቶች፡-
1. ለጨረታ በቀረቡት ዕቃዎች ላይ ለመሳተፍ የሚያስፈልጉ ተጫራች በጨረታ በሚሸጡ ዕቃዎች ጋር በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፍቃድ፣ የተጨማሪ እሴት ታከሰ ምዝገባ ሰርተፍኬት፣ የዘመኑን ግብር የከፈለ ስለመሆኑ ክሊራንስ(Clearance) እና የተጨማሪ እሴት ታክስ እንቅስቃሴያቸውን ለታክሰ ማዕከሉ ያሳወቁበት በቅርብ ጊዜ የተሰጣቸው የምስክር ወረቀት እና የመለያ ቁጥሩን ከመጫረቻ ሰነዱ ጋር አያይዞ በሲስተም አታች ማድረግ ይኖርባቸዋል።
2. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ዘወትር በስራ ሰዓት እስከ ቀን 09/07/2018 ዓ/ም ከኦክሽን ኢትዮጵያ ድረ ገጽ(auction ethiopia page) ማየት ይችላሉ፡፡
3. ለግልጽ ጨረታ ለመሳተፍ ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ዋሰትና (cpo) የሚወዳደሩበትእቃ ኮድ 5 በመቶ አንዲሁም ለሐራጅ ጨረታ ለሚወዳደሩበት አቃ ኮድ ብር 100,000 (አንድ መቶ ሺህ ብር) በባንክ አሰርተው በአዋሽ ጉምሩከ ቅ/ጽ/ቤት ስም በማስያዝ በሲስተም አታች ማድረግ ይኖርባቸዋል።
|
ተ.ቁ
|
አጫራች ቅ/ጽ/ቤት
|
የጨረታው ዓይነት
|
ለጨረታ የቀረቡ እቃዎች
|
የዕቃዎች መመልከቻ የጨረታው ቀን በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ
|
የጨረታው የመዝጊያ እና የመክፈቻ ቀንና ሰዓት
|
|
1
|
አዋሽ ቅ/ጽ/ቤት
|
ግልፅ ጨረታና በሐራጅ
|
ጫማዎች፣ አልባሳት፣ የመኪና መለዋወጫ፣ የሞባይል ቀፎና አክሰሰሪ፣ ኤሌክትሮኒክስ፣ ምግብ ነክ፣ የስፖርት እቃዎች፣ የእጅ ሰዓት፣ ኮስሞቲክስ፣መነፅር እና ሌሎች ልዩ ልዩ እቃዎች
|
ለግልፅና ለሐራጅ ጨረታ በ09/07/2018 እስከ ጠዋቱ 3፡45
|
ለግልጽ ጨረታ በ09/07/2018 ዓ/ም ከጠዋቱ 4፡00 ሲሆን የሐራጅ ጨረታ የመጀመሪያ ጊዜ በ09/07/2018ዓ.ም 5፡00 ሰዓት ይሆናል፡፡
|
4. የጨረታው መክፈቻ ሰዓት እና ቀንን ከኦክሽን ኢትዮጵያ ድረ-ገጽ (auction Ethiopia page) በማየት የጨረታው ሂደት ተጀምሮ ከማለቁ በፊት ዋጋ መስጠት ይችላሉ፡፡
5. ለጨረታው አሸናፊ ተጫራቾች ለጨረታው ዋሰትና ያስያዙት (c.p.O) ከሚከፍሉት ዋጋ ጋር የሚታሰብላቸው ሲሆን ለተሸናፊ ተጫራቾች ደግሞ የጨረታ ውጤት ከተለጠፈበት ቀን ጀምሮ በ3 የስራ ቀናት ውስጥ ተመላሽ ይደረግላቸዋል፡፡
6. ከአሸናፊ ተጫራቾች ማሸነፋቸው በደብዳቤ ከተገለጸላቸው ቀን ጀምሮ በ3 ቀናት ውስጥ ያሸነፈበትን ገንዘብ ገቢ በማድረግ ዕቃውን በመረከብ ከመጋዝን ማውጣት ይኖርበታል፡፡
7. ከላይ በተ.ቁ.6 በተገለጹት ቀናት ውስጥ ክፍያውን ገቢ ያላደረጉ እና ንብረቱን ተረክበው ያልወሰዱ ተጫራቾች ለጨረታው ማሰከበሪያ ያስያዙት ገንዘብ የከፈሉት ዋጋ ለኮሚሽኑ ገቢ ሆኖ ዕቃው በድጋሜ ለሽያጭ ይቀርባል፡
8. ቅ/ጽ/ቤቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
9. የኦክሽን ኢትዮጵያ (auction ethiopia) መተግበሪያን በተመለከተ የጥሪ ማእከሉን ሠራተኛ ለማግኘት በስልክ ቁጥር 09 05 11-55-11/011-66 68 828 በመደወል ማግኘት ይችላሉ።
10. ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 09-13 97-49-27 ይደውሉ።
የአዋሽ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት
