በአ/ብ/መንግሥት በምሥራቅ ጎጃም ዞን የብቸና ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት በ2018 በጀት ዓመት በስሩ ለሚገኙ ሴ/መ/ቤቶች በመደበኛ በጀት ለሚገዙ ሎት-1 የውጭ ሀገር የቤትና የቢሮ ዕቃዎች ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 03
በአ/ብ/መንግሥት በምሥራቅ ጎጃም ዞን የብቸና ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት በ2018 በጀት ዓመት በስሩ ለሚገኙ ሴ/መ/ቤቶች በመደበኛ በጀት ለሚገዙ ሎት-1 የውጭ ሀገር የቤትና የቢሮ ዕቃዎች ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል። ዝርዝር መረጃውንም በጨረታ ሰነዱ ተካቷል ፡፡ በጨረታ ለመሳተፍ ተጫራቾች ማሟላት የሚገባቸው
1. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው
2. የግብር መክፈያ መለያ ቁጥር (TIN NO) ያላቸው
3. የግዥው መጠን ለእቃና አገልግሎት ግዥ ከብር 200,000.00 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ በላይ ከሆነ ተጫራቾች የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው፡፡
4. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ ከተራ ቁጥር 1-3 የተጠቀሱትን ማስረጃዎች ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።
5. ተጫራቾች የእቃዎችን የጨረታ ሰነድ ለመውሰድ የማይመለስ ብር 500 /አምስት መቶ ብር/ በመክፈል መግዛት ይቻላል፣ ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሰነዳቸውን በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድርግ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ለ15 ተከታታይ ቀናት በአየር ላይ የሚውል ሲሆን በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡30 ሰዓት ይታሸግና በዚሁ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ይከፈታል፡፡ ጨረታው ሲከፈት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባይገኙ ሥራውን ከመከፈት አያስተጓጉልም ጨረታው የሚከፈትበት ቀን የበዓል ቀን ከሆነ በተጠቀሰው ሰዓት በሚቀጥለው የስራ ቀን ታሽጎ በተጠቀሰው ሰዓት ይከፈታል፡፡
6. የጨረታ ሰነዱን ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት ብቸና ከተማ አስ/ገንዘብ ጽ/ቤት ግ/ፋ/ን/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 1 መውሰድ የሚቻል መሆኑንና ኦርጅናልና ኮፒን በመለየት በአንድ ፖስታ በማሸግ እስከ 16ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡30 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባችዋል። በተጨማሪ ተጫራቾች የሚጫረቱበትን የሎት ቁጥር፣ ፊርማ፣ ማህተም፣ ስምና አድራሻ በፖስታቸው ላይ እና በሰነዱ ላይ መግለጽ አለባቸው።
7. ከላይ ለተጠቀሰው ሎት ግዥ በእንግሊዘኛ የቀረበ የጨረታ ሰነድ ካለ አሸናፊው ውል ሲይዝ በአማርኛ ማስተርጐም አለበት።
8. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና - ሎት-1 የውጭ ሀገር የቤትና የቢሮ ዕቃዎች ግዥ ብር ብር 75,000.00 /ሰባ አምስት ሺህ ብር/ በባንክ የተረጋገጠ ትዕዛዝ /ሲፒኦ/ ወይም በጥሬ ገንዘብ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማቅረብ አለበት፡፡
9. ከላይ ለተጠቀሰው የእቃ ግዥ አሸናፊ ተጫራቾች አሸናፊነቱ ከተገለጸለት ቀን በኋላ ለውል ማስከበሪያ 10% ዋስትና ከጥሬ ገንዘብ ወይም በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማቅረብ አለበት፡፡
10. መስሪያ ቤቱ አሸናፊነት የሚለየው በጠቅላላ ዋጋ ጥቅል ድምር ዝቅትኛ ዋጋ መሆኑ መታወቅ አለበት።
11. ተጫራቾች ከጨረታ ሰነዱ ጋር የተያያዘውን የተጫራቾች መመሪያ ማየት ይችላሉ፡፡
12. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ አስፈላጊ ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ በማድረግ ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ ይችላሉ፡፡
13. የጨረታ መዝጊያ ከተጠናቀቀ በኋላ ተጫራቾች በአቀረቡት የመወዳደሪያ ሃሣብ ላይ ለውጥ ማድረግና ከጨረታው ራሳቸውን ማግለል አይችሉም፡፡
1. መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
2. ለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 0586651445/0586651446 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል።
የብቸና ከተማ አገ/ገንዘብ ጽ/ቤት
