የሀድያ ዞን ፋይናንስ መምሪያ ለዞኑ ትምህርት መምሪያ የመጀመሪያ ደረጃና የ7ኛ እና የ8ኛ ክፍል የመማሪያ መጽሐፍት ህትመት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለማሳተም ይፈልጋል።
የጨረታ ማስታወቂያ
የሀድያ ዞን ፋይናንስ መምሪያ ለዞኑ ትምህርት መምሪያ የመጀመሪያ ደረጃና የ7ኛ እና የ8ኛ ክፍል የመማሪያ መጽሐፍት ህትመት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለማሳተም ይፈልጋል።
በዚሁ መሠረት ተጫራቾች፡-
1ኛ በመስኩ የታደሰ ንግድ ፈቃድ
2ኛ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር
3ኛ የቫት ተመዝጋቢነት ሠርተፍኬት
4ኛ የዕቃና አገልግሎት አቅራቢነት ሰርትፍኬት ያላቸው ድርጅቶች
በሀድያ ዞን ፋ/ መምሪያ ቢሮ ቁጥር 17 በአካል በመቅረብ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ብር 100 /አንድ መቶ ብር/ በመክፈል እንድትገዙና ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና 100,000 /አንድ መቶ ሺህ ብር/ በባንክ በተረጋገጠ (CPO) “ማስያዝ የሚጠበቅባቸው ሲሆን የጨረታ መወዳደሪያ መምሪያው ባዘጋጀው ፎርማት ላይ ብቻ በመሙላት ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት የመወዳደሪያ ፖስታዎችን ኦርጅናልና ኮፒ በማሽግ ቢሮ ቁጥር 17 ላይ በሚገኘው የጨረታ ሳጥን ውስጥ እንድታስገቡና ጨረታውም በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ላይ የጨረታ ሳጥን ታሽጎ 4፡30 ላይ የሚከፈት ሲሆን ቀኑ የእረፍት ወይም የበዓል ቀን ከሆነ በቀጣዩ ቀን በተመሳሳይ ቦታና ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
መሥሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ:-
ስልክ ቁጥር፡- 0461784281/0465552337 ደውሎ መጠየቅ የሚቻል መሆኑን እንገልጻለን።
በደ/ብ/ብ/ሕ/ክ/መንግሥት የሀድያ ዞን ፋይናንስ መምሪያ
