Tender Detail

Tender Details


በጉለሌ ክ/ከተማ ፖሊስ መምሪያ በ2018 ዓ/ም በጀት ዓመት ለሥራ አገለግሎት የሚውል በዘርፉ ከተሰማሩ ሕጋዊ ከሆኑ አቅራቢዎች ከታች የተዘረዘሩትን ዕቃዎች ሆነ አገልግሎቶችን አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።


የጨረታ ማስታወቂያ

 

በጉለሌ /ከተማ ፖሊስ መምሪያ 2018 / በጀት ዓመት ለሥራ አገለግሎት የሚውል በዘርፉ ከተሰማሩ ሕጋዊ ከሆኑ አቅራቢዎች ከታች የተዘረዘሩትን ዕቃዎች ሆነ አገልግሎቶችን አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

በመሆኑም፡-

1 የተለያዩ የፅዳት ዕቃ

2 የተለያዩ የፅህፈት መሳሪያ

3 ጎሚስታ

4 የመፀዳጃ ቤት ፈሳሽ ማስወገጃ የመኪና ኪራይ

5 ፍራሽ እና ትራስ

6 የሚጫራቱበትን የዕቃ ዝርዝር የሚገልፅ ሰነድ የማይመለስ 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 10 ተከታታይ በሥራ ቀን በጉ//ከተማ ፖሊስ መምሪያ ፋይናንስ ግዥ አስተዳዳር ክፍል ቢሮ ቁጥር 7 ዘወትር በሥራ ሰዓት በመቅረብ መውሰድ ይችላሉ።

7 የሚጫራቱበትን የዕቃ ዋጋ የሚገልፅ ሰነድ በታሸገ ኤንቨሎፕ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ እስከ ከቀኑ 1100 ሰዓት ባለው ጊዜ ውስጥ ለዚህ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን አስገብቶ ይታሸጋል

8 ተጫራቾች በተሰማሩበት የሥራ መስክ የዘመኑ ግብር ለመክፈላቸው ማረጋገጫ ማቅረብ አለባቸው።

9 ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት ዕቃዎች ናሙና ከጨረታ መክፈቻ ቀናት አስቀድመው ማቅረብ ለሚችሉባቸው ዕቃዎች አንድአንድ ናሙና ማቅረብ አለባቸው

10 ተጫራቾች በገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር ወይም ከአ/አበባ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት የቢሮ ዕቃ አቅራቢዎች ዝርዝር ገፅ የተመዘገቡ ለመሆናቸው የምስክር ወረቀት አያይዘው ማቅረብ አለባችው።

11 ተጫራቾች ከሚያቀረቡት ዋጋ በእያንዳንዱ ሎት ማለትም ተራ ቁጥር 1 እስከ………ድረስ ያሉትን ዕቃዎች የጨረታ ማስከበሪያ 3,000.00 /ሶስት ሺህ ብር/ በባንክ የተረጋገጠ CPO ብቻ ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ማስያዝ ይኖባቸዋል።

12 አሸናፊው አሸናፊነቱ እንደተገለፀለት ወዲያው ለአሸነፈበት ጠቅላላ ዋጋ 10% የመልካም ሥራ አፈፃፀም ዋስትና CPO ብቻ ማስያዝ ይኖርበታል።

13 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይህ ማስታወቂያ በተጠናቀቀበት 10ኛው የሥራ ቀን በመ/ቤቱ የስብሰባ አዳራሽ በዛው ዕለት በቀኑ 1100 ሰዓት ታሽጎ 11ኛው ቀን ከጠዋቱ 330 ሰዓት ተጫራቾቹ ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጨረታው ይከፈታል። ቀኑ በሥራ ቀን ካልዋለ በሚቀጥለው በሥራ ቀን 330 ሰዓት ጨረታው ይከፈታል።

14 አማራጭ ዋጋ በዚህ ጨረታ ማቅረብ ወይም መጠቀም አይቻልም።

15 መስሪያ ቤቱ በግዥ ወቅት 25% መጨመር መቀነስ ይችላል።

16 መስሪያ ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

 

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር፡- 011 156 6407/ 09 44 07 63 24/ 09 20 29 88 66

 

ጉለሌ /ከተማ ፖሊስ መምሪያ

Save Tender