Tender Detail

Tender Details


በቾ ወሊሶ የገበሬዎች ሕብረት ሥራ ዩኒየን የተለያየ ዓይነት የምጥን ማዳበሪያ ፋብሪካ ግብዓቶች በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።


ለሁለተኛ ጊዜ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ

 

በቾ ወሊሶ የገበሬዎች ሕብረት ሥራ ዩኒየን የተለያየ ዓይነት የምጥን ማዳበሪያ ፋብሪካ ግብዓቶች በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል። በመሆኑም እነዚህን ግብዓቶች መግዛት የሚፈልጉ ግለሰቦች ወይም ድርጅት ከዚህ ቀጥሎ ያሉትን መስፈርቶች በማሟላት ተወዳድራችሁ መግዛት የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን።

ተጫራቾች ማሟላት ያለባቸው መመዘኛዎች፡-

1.     ህጋዊ የንግድ ፍቃድ ያለው እና የዓመቱን ግብር የከፈለ።

2.     ለጨረታ ሰነድ ግዢ የማይመለስ ብር 500 (አምስት መቶ) በዩኒየኑ የባንክ ሂሳብ ቁጥር 1000087184327 ኦሮሚያ ህብረት ስራ ባንክ ወይም የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 1000036818348 በመክፈል ሰነዱን ከዩኒየን መውሰድ አለባቸው።

3.     ለጨረታ ማስከበሪያ ቢድ ቦንድ ማስያዣ ያቀረቡትን ዋጋ 5% በሲፒኦ ወይም በባንክ ዋስትና ሰነድ ማስያዝ አለባቸው።

4.     ተጫራቾች ይህ ጨረታ ከወጣ ቀን ጀምሮ እስከ 19/08/2018 ከጠዋቱ 400 ሰዓት ድረስ የጨረታ ሰነዶቹን በታሸገ ኤንቨሎፕ ዘወትር በሥራ ሰዓት ዩኒየኑ ባዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት አለባቸው።

5.     የጨረታ መክፈቻ ቀን 19/08/2018 ሳጥኑ ከጠዋቱ 400 ሰዓት ተዘግቶ 430 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።

6.     ተጫራቾች አንዱ ተጫራች በቀረበው ዋጋ ላይ ተንተርሰው ዋጋ ማቅረብ የተከለከለ ነው።

7.     ዩኒየኑ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

8.     አሸናፊው ተጫራች ያሸነፈውን ንብረት ሙሉ በሙሉ እስከ 10 ቀን ጊዜ ውስጥ ማንሳት ይኖርበታል።

አድራሻ - በጅማ መንገድ ከአዲስ አበባ 80 . ቱሉ ቦሎ ከተማ ላይ እንገኛለን።

ለተጨማሪ ማብራሪያ፡- በስልክ ቁጥር 0911 08 00 03 / 0912 12 29 71 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል።

 

 

የበቾ ወሊሶ የገበሬዎች ሕብረት ሥራ ዩኒየን ኃላፊነቱ የተወሰነ ማህበር

Save Tender

በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የኢንጂነሪንግና ኮንስትራክሽን ቢዝነስ ዘርፍ ፋይናንስ እና ግዥ መምሪያ Core Drilling Machine with spare part...

READ MORE