Tender Detail

Tender Details


የቦዲቲ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የ2018 ዓ.ም የሥልጠና ዕቃዎችን ሎት 1 Auto ሎት 2 የደንብ ልብስ ሎት 3 ICT ሎት 4 IEMDS ሎት 5 BEI ሎት 6 Masonary ሎት 7 GMFA Metal Manufacturing ሎት 8 Stationary አላቂ የቤትና የቢሮ ዕቃ ሎት 9 ቋሚ የቤትና የቢሮ ዕቃዎችን ጨምሮ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።


ለሁለተኛ ዙር የወጣ የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

 

የቦዲቲ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን 2018 . የሥልጠና ዕቃዎችን ሎት 1 Auto ሎት 2 የደንብ ልብስ ሎት 3 ICT ሎት 4 IEMDS ሎት 5 BEI ሎት 6 Masonary ሎት 7 GMFA Metal Manufacturing ሎት 8 Stationary አላቂ የቤትና የቢሮ ዕቃ ሎት 9 ቋሚ የቤትና የቢሮ ዕቃዎችን ጨምሮ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

ስለዚህ፡- በዘርፉ ማለትም 2018 . የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያለው፣ የግብር መለያ ቲን ሰርተፍኬት ያለው፤ የቫት ተመዝጋቢ የሆነና የግብር ግዴታቸውን ስለመወጣታቸው በቂ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉና በመንግስት ጨረታ ላይ እንድሳተፉ የዕቃ አቅራቢነት ፈቃድ /የምስክር ወረቀት ያላቸው ሆኖ ከዚህ በታች በተዘረዘረው መሰረት ማለትም የጨረታ ሰነድ ለመግዛት ለእያንዳንዱ ሰነድ /ሎት/ የማይመለስ ብር 300.00 /ሶስት መቶ ብር/ ብቻ በመክፈል ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ በቦዲቲ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ቢሮ ቁጥር 108 በመምጣት ሰነዱን በመግዛትና በቦታው በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ የጨረታ ሰነዱን መጨመር የምችሉ መሆኑን እየገለጽን፦

*         ተጫራቾች የሚመረቱበትን ጠቅላላ ዋጋ ከቫት ጭምር መሙላት አለባቸው።

*         ተጫራቾች በእያንዳንዱ ሎት 5,000.00 /አምስት ሺህ/ ብር የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ CPO ማስያዝ አለባቸው።

*         ጨረታው በታሸገ ኤንቨሎፕ እያንዳንዱ ሰነድ በሁለት ኮፒ ከዋናው ሰነድ ጋር በሦስት ኤንቨሎፕ / ፖስታ መቅረብ አለበት።

*         የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀኖች ከፍት ሆኖ ከቆየ በኋላ 16ኛው በሥራ ቀን ከጠዋቱ 400 ሰዓት ታሽጎ ከጠዋቱ 430 ሰዓት ወይም የሥራ ቀን ካልሆነ ቀጥሎ ባለው በሥራ ቀን በተባለው ሰዓት ላይ በቦዲቲ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ቢሮ ቁጥር 108 ተጫራቾች ወይንም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።

*         ጨረታውን ያሸነፉ ተወዳዳሪዎች ላሸነፉበት ዕቃ ዋጋው ተሰልቶ የጨረታ ውል ማስከበሪያ 10% ማስያዝ ይኖርባቸዋል።

*         ተጫራቾች ያሸነፉበትን ዕቃ ከሚሰጣቸው ጊዜ ገደብ ውስጥ ውል ገብተው እስከ ኮሌጁ ቅጥር ግቢ ድረስ ጊዜ ካላቀረቡና ውል ለመግባት ፈቃደኛ ካልሆነ ያስያዙት CPO ይወረሳል።

ማሳሰቢያ፡- ማንኛውም ተጫራቾች የጨረታውን ስፔስፊክሽን መቀየርና በሰነድ ላይ ስርዝ ድልዝ ካደረጉ ያቀረቡት የጨረታው ሰነድ ውድቅ እንደሚደረግ ማወቅ አለባቸው።

*         ኮሌጁ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ግን ጨረታውን መሉ በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

*         ይህ ጨረታ ጸንቶ የሚቆየው ጨረታው ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ 60 ቀናት ብቻ መሆኑንም እንገልጻለን።

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 09 11 97 85 88 መደወል ይቻላል።

 

በደ/ ክልላዊ መንግስት ////ቢሮ የቦዲቲ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ

Save Tender