Tender Detail

Tender Details

  • Company Addis Ababa University (አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ)
  • Address 6ኪሎ ዋናው ግቢ : አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 011-1-22-00-01
  • Websitehttps://www.aau.edu.et/
  • Deadline14 May 2026, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price200.00
  • opening date2026-05-14 00:00:00
  • Categories Land, House, Building And Warehouse Rent

አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በዋናው ግቢ ፎረም ህንጻ ያሉ ቦታዎችን ለተለያዩ አገልግሎቶች (ለመፃህፍት ቤት፤ ለስቴሽነሪ እና ለቢሮ አገልግሎት) በግልጽ ጨረታ ለማከራየት ይፈልጋል፡፡


የንግድ ቤቶች ኪራይ የጨረታ ዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ

የግዥ ቁጥር- አአዩ/ብግ/የሱቅ ኪራይ/006/2018/26

 

1.     የተጫራጭ ስም  - - - - - - - - -

2.     የተጫራች አድራሻ - - -  አዲስ አበባ - - - - /ከተማ ወረዳ - - - የቤት ቁጥር - - - ስልክ ቁጥር - - -

3.     የንግድ ፈቃድ ቁጥር - - -

4.     ቲን ሰርተፍኬት ቁጥር - - -

5.     የስራው አይነት - - -

6.     የሚጫረቱበት ፍል ቁጥር - - -

7.     ተጫራቾች የሚጫረቱበት የአንድ ካሬ ሜትር ዋጋ ቫትን ጨምሮ - - -

ማሳሰቢያ፡-

1.     አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በዋናው ግቢ ፎረም ህንጻ ያሉ ቦታዎችን ለተለያዩ አገልግሎቶች (ለመፃህፍት ቤት፤ ለስቴሽነሪ እና ለቢሮ አገልግሎት) በግልጽ ጨረታ ለማከራየት ይፈልጋል፡፡

2.     ተጫራቾች የጨረታ ሠነዱን ከታች በተገለፀው አድራሻ ግንቦት 06 ቀን 2018 . እስከ 400 ሰአት ድረስ ጨረታውን ለያዘው ሰው ማሰረከብ ወይም ለዚህ ጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ማስገባት ይችላሉ፡፡ ዘግይተው የቀረቡ የጨረታ መልሶች ተቀባይነት የላቸውም፡፡ በጨረታው ላይ ለመገኘት በፈለጉ ተጫራቾች ወይም የተጫራቾች ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ግንቦት 06 ቀን 2018 . 430 ሰአት ይከፈታል፡፡

3.     ከዚህ የጨረታ ሰነድ ጋር የታደሰ ንግድ ፈቃድ እና ቲን ሰርተፍኬት መያያዝ አለበት፡፡

4.     የጨረታ አሸናፊዎች የኪራይ ውል መዋዋል የሚችሉት ለጨረታ ባስገቡት የንግድ ፈቃድ ስም ብቻ ነው፡፡

5.     በጨረታ ያሸነፉበትን ክፍል በምንም ዓይነት ለሌላ ወገን ስም ማዞርም ሆነ ተከራይቶ ማከራየት የማይቻል ሲሆን ይህንን ለማድረግ የሚሞከሩ ተጫራቾች ከጨረታ ውጪ እንደሚሆኑ እና የኪራይ ውሉ እንደሚሰረዝ ለማሳሰብ እንወዳለን፡፡

6.     ፍላጎት ያላቸው ተጫራቾች የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ለመግዛት ከዚህ በታች በተገለፀው አድራሻ የማይመለስ የኢትዮጵያ ብር 200.00 (ሁለት መቶ ብር) በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሂሳብ ቁጥር 1000087392067 ገቢ በማድረግ የባን ደረሰኝ ይዘው በመምጣት የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ

7.     ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ የጨረታ ማስከበሪያ መጠን ብር በሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንከ ዋስትና አያይዘው 50,000.00 (ሃምሳ ሺህ ብር) ማቅረብ አለባቸው፡፡

8.     ይህ የጨረታ መጋበዣ ሰነድ የሚያካትታቸው ዋና የሚከራዩ ቦታዎች ዝርዝር እና የሚከራይ ቦታውን የሚያሳይ ዲዛይን ይሆናል፡፡

9.     ይህ የኪራይ አገልግሎት ጨረታ ታሳቢ የሚያደርገው በሀገር ውስጥ ለሚፈፀም የአገልግሎት ሽያጭ (የም አገልግሎት አይጨምርም) የሚውል መደበኛ የጨረታ ሰነድ ይሆናል፡፡

10. ዩኒቨርሲቲው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው

 

የጨረታ ሰነዱ የሚሸጥበት አድራሻ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ 6 ኪሎ ዋናው ግቢ የአስተዳደር ህንፃ ግዥ አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር፡- 314 ስልከ ቁጥር፡- 251+111243290

 

አዲስ አበ ዩኒቨርሲቲ

 

Save Tender