Tender Detail

Tender Details

  • Company የአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ ጤና ቢሮ የሳሪስ ጤና ጣቢያ
  • Address ሳሪስ 3F ፊት ለፊት ከሙኒክ ሆቴል አጠገብ : አዲስ አበባ ፡ ኢትዯጵያ, Phone: 0114-70-98-59
  • Website
  • Deadline12 May 2026, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price
  • opening date2026-05-12 00:00:00
  • Categories Used Items

በአቃ/ቃ/ክ/ከተማ ሳሪስ ጤና ጣቢያ ያገለገሉ እቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።


ያገለገሉ እቃዎች ሽያጭ ጨረታ ቁጥር 03/2018

 

በአቃ///ከተማ ሳሪስ ጤና ጣቢያ ያገለገሉ እቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።

 

በአቃ////ወረዳ 6 ልዩ ቦታ ሳሪስ ጤና ጣቢያ አደይ አበባ ሙኒክ ሆቴል ፊት ለፊት የሚገኝ ሲሆን የተለያዩ ያገለገሉ 31 አይነት በላይ እቃዎች አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል። እቃዎቹ የሚገኝበት ሳሪስ ጤና ጣቢያ ግቢ ውስጥ ሆኖ የዋጋ መሙያ ሰነድ እና የጨረታ ሳጥን ቢሮ ቁጥር 35 ይገኛል። ማንኛውም ተጫራች ጋዜጣው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 10 ቀናት የጨረታ ሰነዱን ከሳሪስ ጤና ጣቢያ ከፋ ቡድን ቢሮ ቁጥር 35 የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል መውሰድ የምትችሉ መሆኑን እየገለፅን ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ዋጋ ማለትም ያገለገሉ የቢሮ እቃዎች ሽያጭ 3,000.00 (ሶስት ሺህ ብር) በሲፒኦ (CPO) በአድራሻችን ከጨረታ ሰነድ ጋር በፖስታ በማሸግ ማቅረብ አለባቸው። የጨረታ ሰነድ ጨረታ ሳጥን ውስጥ ከገባ በኋላ እና አሸናፊው ድርጅት አሸናፊ መሆኑን በደብዳቤ ከተገለፀለት ቀን ጀምሮ ከውድድሩ ቢወጡ የጨረታ ማስከበሪያ ለመንግስት ገቢ ይሆናል። ጨረታው ጋዜጣ ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 10ኛው ቀን አየር ላይ ውሎ 11ኛው ቀን ከጠዋቱ 400 ሰዓት ላይ ታሽጎ በዛኑ ቀን ከጠዋቱ 430 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸቸው ባሉበት ሳሪስ ጤና ጣቢያ ካርድ ክፍል ፊት ለፊት ባለው አዳራሽ ይከፈታል፡፡ ነገር ግን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባይገኙም የጨረታ መክፈት ሂደት በተቀመጠው መሰረት ይካሄዳል። የጨረታ መዝጊያ እና መክፈቻ ቀን ዝግ ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ይሆናል። ተጫራቾች ከመስሪያ ቤቱ በገዙት የጨረታ ሰነድ ላይ ብቻ የዋጋ ዝርዝር ሞልተው ማቅረብ አለበቸው። አሸናፊ የሚሆነው ድርጅት ወይም ግለሰብ በጠቅላላ ዋጋ ብልጫ ያለው ብቻ ነው። አሸናፊው ተጫራች ማሸነፉን በደብዳቤ ከተገለፀለት ቀን ምሮ 3 ቀናት ውስጥ ያሸነፈበትን ገንዘብ መስሪያ ቤቱ በሚያዘው የክፍያ አማራጭ ገቢ በማድረግ እቃውን ከቦታው ማንሳት ያለበት ሲሆን ይህ የማይሆን ከሆነ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዘው ዋስትና የሚወረስ ይሆናል። ይህ ጨረታ የታካሚዎች ካርድ ማስወገድን ስለሚያካትት ማንኛውም አሸናፊው ድርጅትም ሆነ ግለሰብ የታካሚዎችን ካርድሙሉ በሙሉ ሪሳይክል ወይም የሚወገድበት ዘዴ በፋብሪካ ተፍጭቶ ወደ ሌላ አገልግሎት የሚውል መደረጉን ተቋሙ ያዋቀረው ኮሚቴ በቦታው ላይ ሄዶ ሪሳይክል መደረጉን ለማሳየት ፈቃደኛ መሆን ግዴታ አለበት። አሸናፊ የሚሆነው ድርጅት/ግለሰብ ጠቅላላ ድምር ብልጫ ያለው ስለሆነ እቃውን በሙሉ ማንሳት አለበት። /ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

 

አድራሻ፡- አቃ////ወረዳ 06 ሳሪስ ጤና ጣቢያ 3F ፊት

ለፊት ከሙኒከ ሆቴል አጠገብ ስልክ፡- 0114-70-98-59/0114-707977

 

በአዲስ አበባ ከተማ ጤና ቢሮ የአቃቂ ቃሊቲ /ከተማ ጤና /ቤት የሳሪስ ጤና ጣቢያ

Save Tender