የሀድያ ዞን ፋይናንስ መምሪያ በዞኑ ለሚገኙ ሴክተር መ/ቤቶች የሚያስፈልጉ የተለያዩ ዓይነት፡ የፈርኒቸር ዕቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
በድጋሚ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ
የሀድያ ዞን ፋይናንስ መምሪያ በዞኑ ለሚገኙ ሴክተር መ/ቤቶች የሚያስፈልጉ የተለያዩ ዓይነት፡ የፈርኒቸር ዕቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
በዚሁ መሠረት ተጫራቾች፡-
1ኛ. በመስኩ የታደሰ ንግድ ፈቃድ
2ኛ. የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር
3ኛ. የቫት ተመዝጋቢነት ሠርትፍኬት
4ኛ. የዕቃ አቅራቢነት ሰርትፍኬት ያላቸው ድርጅቶች
በሀድያ ዞን ፋ/መምሪያ ቢሮ ቁጥር 17 በአካል በመቅረብ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ብር 200 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል እንድትገዙና ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና 30,000 ብር በባንክ የተረጋገጠ (CPO) ማስያዝ የሚጠበቅባቸው ሲሆን የጨረታ በመሙላት ይህ የጨረታ ማስታወቂያ መወዳደሪያ መምሪያው ባዘጋጀው ፎርማት ላይ ብቻ በመሙላት ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ ቀናት የመወዳደሪያ ፖስታዎችን ኦርጅናልና ኮፒ በማሸግ ቢሮ ቁጥር 17 ላይ በሚገኘው የጨረታ ሳጥን ውስጥ እንድታስገቡና ጨረታውም በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ላይ የጨረታው ሳጥን ታሽጎ በ4፡30 ላይ የሚከፈት ሲሆን ቀኑ የእረፍት ወይም የበዓል ቀን ከሆነ በቀጣዩ ቀን በተመሳሳይ ቦታና ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
መሥሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ፡- በስልክ ቁጥር
0461784281 / 0465552337 ደውሎ መጠየቅ የሚቻል መሆኑን እንገልጻለን።
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግሥት የሀድያ ዞን ፋይናንስ መምሪያ
