Tender Detail

Tender Details

የኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን የተለያዩ ያገለገሉ የቢሮ ዕቃዎች፣ ያገለገሉ ጎማዎች፣ ቁርጥራጭ፣ ብረታ ብረት፣ ቁርጥራጭና ብትን ጨርቃ ጨርቆች፣ የወንድና የሴት ጫማዎች፣ የተለያዩ ኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች ያገለገሉ በርሜሎች፣ ያገለገሉ የነዳጅ ማከማቻ ታንከር ፣ ያገለገሉ ኮንቴነሮች በጨረታ አወዳደሮ መሸጥ ይፈልጋል።

የጨረታ ማስታወቂያ

1.     ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200 / ሁለት መቶ / በመክፈል ከንብረት አስተዳደር ቢሮ ማግኘት ይችላሉ።

2.     ተጫራቾች የሚገዙበትን ዋጋ በታሸገ ፖስታ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ከንብረት አስተዳደር ቢሮ በመገኘት በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ።

3.     ጨረታው ግንቦት 18 ቀን 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ቀን ከጥዋቱ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በኮርፖሬሽኑ የስብሰባ አዳራሽ የሰነድ የመክፈቻ ሥነ ስርዓት ይከናወናል።

4.     ተጫራቾች ለጨረታ ዋስትና ተመላሽ የሚደረግ ብር 50,000.00 /ሃምሳ ሺህ/ ሲፒኦ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።

5.     ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

አድራሻ: ሳሪስ አቦ ፋፋ የምግብ አክሲዮን ጎን 200 ሜትር ገባ ብሎ

በስልክ ቁጥር : 09 60-28 79 03 ፣ 09 13- 97 37 99 ፣ 09 11-16 64 73

ማሳሰቢያ ፡- ያገለገሉ ዕቃዎችን ዘውትር በሥራ ሰዓት የጨረታ ሰነዱን የገዙ ሰዎች ብቻ ንብረቱን መመልከት ይችላሉ

የኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን

Save Tender